የብልጽግና ፓርቲ አመራርና አባላት ህዝቡ የጣለባቸው ኃላፊነትና ተግባር በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው የጉራጌ ዞን የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ገለፀ ።


የብልጽግና ፓርቲ አመራርና አባላት ህዝቡ የጣለባቸው ኃላፊነትና ተግባር በአግባቡ በመወጣት የህዝቡን ሠላም፣ ደህንነት፣ ልማትና እድገት ማፋጠን አለባቸው ተባለ።

ፓርቲው በባለፉት 4 ተከታታይ ቀናት በአመራርና አባላት ግንባታና ማጥራት እንዲሁም በቀጣይ ተልዕኮዎች ዙሪያ ሲያካሄድ የነበረው የዞን መድረክ መጠናቀቁ ተገልጿል።

የጉራጌ ዞን ለብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ክፍሌ ለማ በሰጡት መግለጫ ሀገራዊ ለውጡ አጠናክሮ ለማስቀጠልና ህዝቡ የሚያነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር እንዲሁም ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ አሁን ያለው አመራርና አባላት ግንባር ቀደም ሆነው ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ተናግረዋል ።

የተጀመረው የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ አሁን ያለው አመራርና አባላት የሚስተዋሉ መልካም አፈፃፀሞችን ይበልጥ በማጠናከር ጉድለቶችን ደግሞ ለይቶ በመፍታት የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማጎልበት ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ አለባቸው ተብለዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ምርጫው ስኬታማ እንዲሆን፣ የህዳሴው ግድብና ሌሎች ትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ ህወሃት የከፈተብን ጦርነት በመመከትና አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ በማድረግ ከፍተኛ ርብርብ ሲያደርግ መቆየቱን የገለፁት አቶ ክፍሌ በቀጣይ ለውጡን ለማስቀጠል ያላሰለሰ ጥረት እንደሚደረግ ገልፀዋል።

ድርጅቱ በምርጫው ወቅት በገባው ቃል መሰረት በርካታ ሊሰሩ የሚገቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች እንዳሉ መላው የዞኑ አመራርና አባላት አውቆ ለስኬታማ እንቅስቃሴና ውጤት እራሱን ማዘጋጀትና መተግበር አለበት ብለዋል።

ለተከታታይ 4 ቀናት የተካሄደው መድረክ በዞን፣ በወረዳ፣ በከተማ አስተዳደር እንዲሁም በቀበሌ ደረጃ ያለው የፓርቲው የውስጥ አሰራር ውስንነቶች ለመፍታት፣ የአመራርና አባላት ግንባታ ሂደት ለማጠናከርና የስራ አፈፃፀም ክፍተቶችን ለመሙላት እና የህዝቡ የልማት የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያስችል መድረክ እንደነበር ተናግረዋል።

በዚሁ መሰረት በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የአመራርና አባላት ግንባታና ማጥራት ውይይት መድረኮች መጀመሩና እስከታች ቀበሌ ድረስ እንደሚርድ ገልፀዋል።

በሀገር ብሎም በዞኑ ደረጃ የተጀማመሩ የልማትና የለውጥ ጉዞ ከዳር ለማድረስና የህብረተሰቡ ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ፓርቲው የሚያደርገው ርብርብ ውጤት እንዲያመጣ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በተለይም አመራሩና አባላቱ ግንባር ቀደም ሆኖ ሊያግዝ እንደሚገባ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሻሻል፣ የመንግስትና የብልጽግና ፓርቲ ተግባርና ኃላፊነቶች ውጤታማ እንዲሆኑ ርብርብ እንዲያደርጉ ሲሉ አስገንዝበዋል መግለጫውን ተከታትሎ የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *