የቡኢ ኮንስትራክሽን እና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በደረጃ ሁለት እና አራት ያሰለጠናቸውን 196 ተማሪዎች የምረቃ ስነ ስርአት በዛሬው እለት አካሄዷል።

መስከረም 22/2015ዓ.ም

የቡኢ ኮንስትራክሽን እና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በደረጃ ሁለት እና አራት ያሰለጠናቸውን 196 ተማሪዎች የምረቃ ስነ ስርአት በዛሬው እለት አካሄዷል።

የቡኢ ኮንስትራክሽን እና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ከተመሰረ ጀምሮ ከ6መቶ በላይ ሰልጣኞች በዝቅተኛ እና መካከለኛ ደረጃ አሰልጥኖ አስመዝኖ አስመርቆ ወደ ስራ አለም እንዲቀላቀሉ አድርጓል።
የኮሌጁ ዲን አቶ ሙልጌታ ሞላ በምረቃ ስነ ስርአቱ ባስተላለፉት መልእክት መመረቅ ለቀጣይ ጉዞአችን የክህሎት ስልጠና እና የብቃት የምዘና ሰርተፍኬት ተይዞ የሚወጣበት ዕለት ቢሆንም ተመራቂዎች ስራ ፈላጊዎች ሳትሆኑ ስራ ፈጣሪ በመሆን ለሌሎች የስራ እድል በመፍጠር በመደራጀት መንግስት በሚያመቻቸው የብድር እና የመሸጫ ቦታና የገበያ ትስስር ምቹ እድል መጠቀም ይገባል ብለዋል።ሀገሪቱ እያደረገች ባለው ወደ ኢንዱስትሪ መር የኢኮኖሚ ሽግግር ተዋናይ መሆን አለባቸው።

በጉራጌ ዞን የቡኢ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እና የኮሌጁ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ይሽልጌታ በላይነህ እንዳሉት የቡኢ ኮንስትራክሽን እና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የገበያ ፍላጎት መሰረት በማድረግ ምርታማ በራስ የሚተማመን ብቁ ተወዳዳሪ ስራ ፈጣሪ ዜጎች በጥራትና በብዛት በማፍራት ሀገራችን ለምታደርገው የብልፅግና ጉዞ የበኩሉ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑ ማሳያ ነው።

ሀገራችን ከድህነት እና ኃላቀርነት ለማላቀቅ የኢኮኖሚያዊ መዋቅር ለውጥ ለማድረግ በቴክኒክ ሙያ ተቋማት ሰልጥነው የሚወጡ ተመራቂዎች በተለይ በኮንስትራክሽን ና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ ሰልጣኝ ተመራቂዎች ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ።
ተመራቂዎች በተሰማሩበት የግልም ሆነ የመንግስት ስራ አርአያ በመሆን በቀጣይ የትምህርት ጊዜአቸው የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንዳለባቸው አስረድተዋል።

የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ ስልጠና መምሪያ ኮሌጅ ኃላፊ አቶ አብዱ አህመድ እንደገለፁት ሀገራችን ኢትዮጵያ ህዳሴዋን ለማረጋገጥ በተዘረጋው ፖሊሲ ለወጣቶች ለሴቶች ለአካል ጉዳተኛች ስራ ፈላጊ ዜጎች እውቀት ክህሎት እና አመለካከት በተገቢው በመቅረፅ ከስልጠናው በኃላ ወደ ስራ እንዲሰማሩ በማድረግ ወደ ኢንዱስትሪ ሽግግር በማፋጠን ውጤታማ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

የደቡብ ክልል ቴክኒክ ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መዝረዲን ሁሴን በምረቃ ፕሮግራሙ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ በሀገሪቱ ያሉ ወጣቶች አእምሮአቸው ከስራ ጋር በማላመድ ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

ኮሌጆቻችን የኢንዱስትሪያሊስት መፈልፈያ ማድረግ ኢኮኖሚያችንን የበለጠ እንዲደግፉ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በሀገር ውስጥ እንዲመረቱ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመጨረሻም ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የሽልማትና ኮሌጁን ሲያግዙ ለነበሩ ባለድርሻ አካላት የእውቅና ፕሮግራም ተካሂዷል። መረጃው የሶዶ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *