የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር በሁለተኛው የከተሞች መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገብ የደረቅ ቆሻሻ ማንሻ ተሽከርካሪ ሽልማት ተበረከተለት።

በሁለተኛው የከተሞች መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ 15 ከተሞች የደረቅ ቆሻሻ ማንሻ ተሽከርካሪ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር በፌደራል ደረጃ የተሻለ አፈፃፀም ካስመዘገቡ ከተሞች አንዱ በመሆኑ ሽልማቱ የተበረከተለት ሲሆን የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ነስሩ ጀማል በሽልማት ስነ-ስርዓቱ ተገኝተው ቁልፍ ተቀብለዋል።

በስነስርአቱ ላይ የተገኙት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እንደገለጹት በሁለተኛው የከተሞች መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም በተለያዩ መመዘኛዎች የተሻለ አፈጻጸም ላሳዩ 15 የኢትዮጵያ ከተሞች ከ51 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የወጣባቸውን የደረቅ ቆሻሻ ማንሻ ማሽን ተበርክቶላቸዋል።

ይህ እውቅና ከተሞች በቀጣይ ጤናማ የፉክክር መንፈስ በመፍጠር ጥሩ ስራ እንዲሰሩ ያበረታታል ብለዋል።

የኢትዮጵያ የከተሜነት ምጣኔ እየጨመረ መጥቷል ያሉት ሚኒስትሯ፣ በርካታ ችግሮችን ለመቅረፍ እየተሰራ ቢሆንም አሁንም የመሰረት ልማት፣ የስራ አጥነት፣ የህብረተሰብ አያያዝና መሰል ችግሮች መኖራቸውን ገልጸዋል።

የከተማ መሰረት ልማት በመንግስት አቅም ብቻ መቅረፍ የማይቻል በመሆኑ ከአበዳሪ አካላት ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

ተሽከርካሪው የተበረከተላቸው ከተሞችም ቡታጅራ፣ደሴ፣ ደብረታቦር፣ ባህርዳር፣ ቢሾፍቱ፣ ነቀምቴ፣ ጂማ፣ ጅጅጋ፣ ሀዋሳ፣ሆሳእና፣ ሰመራ-ሎጊያ፣ አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ ሀረርና ድሬዳዋ ናቸው ሲል ኢ.ፕ.ድ ዋቢ አድርጎ መረጃው ያደረሰን የከተማው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገጻችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *