የበጋ ስንዴ የመስኖ ልማት ስራ ውጤታማ መሆኑን በጉራጌ ዞን የቸሃ ወረዳ አስተዳደር ገለፀ።

የወረዳው ድጋፍና ክትትል የተሻለ ውጤት ለማምጣት እንዳስቻለ በበጋ መስኖ ተሰማርተው የሚያለሙ የወረዳው አርሶ አደሮች ተናገሩ ።
የቸሀ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙራድ ከድር እንደገለጹት እንደ ሀገር እየተስተዋለ ያለውን የምርት እጥረት ለመቅረፍ ከፍተኛ ሚና የሚጫወተውን የበጋ መስኖ ስራን ውጤተማ ለማድረግ አመራሩና የግብርና ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነዉ።
በወረዳው የውሃ አማራጮች ባሉባቸው ቀበሌዎች ሁሉ በመስኖ ስንዴና የተለያዩ የጓሮ አትክልቶችን ሞዴል አርሶ አደሮችና የተደራጁ ወጣቶችን በሰፋት በማሳተፍ እየለማ መሆኑን ገልፀዋል ።
ለስራው አስፈላጊ የሆኑ 48 ጀነሬተሮችና ሌሎች ግብዓቶችን በማቅረብ እንዲሁም በቂ የቅደመ ዝግጅት ስራ በማከናወን ወደ ተግባር በመገባቱ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል።
በወረዳው በመደበኛና በበጋ መስኖ ልማት የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠልና የግብርናው ዘርፍ በማዘመን የአርሶ አደሩ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ይሠራል ብለዋል።
ያሉ የውሃ አማራጮችን በመለየት፣ በቂ የግብዓት ዝግጅት በማድረግና የአርሷ አደሩን ጊዜናና ጉልበት በመጠቀም ከዚህ ቀደም የማይቻል የሚመስል የነበረው የበጋ ሰንዴ ልማት እውን ማድረግ ተችሏል ብለዋል።
የቸሃ ወረዳ የግብርና ልማት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ይለማ በወረዳዉ 3ሺህ 3መቶ 10 ሄክታር ማሳ በስንዴ፣በቲማቲም፣ በጓሮ ጎመን እንዲሁም በበጋ መስኖ መሸፈን መቻሉን ገልፀዋል።
በወረዳው ከየተኛውም ጊዜ በተሻለ መልኩ የበጋ መስኖ ውጤተማ ለማድረግ የተሻሻሉ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግና ሌሎች ከዚህ ቀደም ይገጥሙ የነበሩ ችግሮች ለመቅረፍ በየደረጃው ካሉ ባለድርሻ አካለት ጋር በቅንጅት አየተሠራ ነው ብለዋል።
በምግብ እራሳችንን በመቻል ከውጭ የሚገባውን ስንዴ ለማስቀረት እንደ ሃገር የተጣለው ግብ ለማሳካት በወረዳው የበጋ መስኖ ስንዴ ውጤተማ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው ያሉት አቶ ዮሴፍ የውሃ አቅምን መሠረት ባደረገ መልኩ በ7 ቀበሌዎች ሞዴል አርሶ አደሮችንና ወጣቶችን የማሳተፍ ስራ ተሠርቷል ብለዋል።

የወረዳው የግብርና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሴፋ ይለማ እንደገለፁት የበጋ ስንዴን ለማምረት በወረዳው በተመረጡ አካባቢዎች የታየው ተስፋ ሰጪ ውጤት በመሆኑ በቀጣይ የውሃ አቅሙን መሠረት በማድረግ በሁሉም ቀበሌያት የማስፋት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ።
ከዚህ ቀደም የበጋ መስኖ ልማት በአካባቢያቸው ለማስለመድ በርካታ ተግዳሮቶች የነበሩ ቢሆንም አሁን ላይ በወረዳው በተደረገው የጋራ ርብርብ የተሻለ ምርት ለማግኘት በሚያስችል ደረጃ ስራ መሠራቱን አብራርተዋል ።

የወረዳው መንግሥት ከባለድርሻ  አካላት ጋር በመቀናጀት ባደረገላቸው የጀነሬተር ና የግብዓት እንዲሁም የክህሎት ድጋፍ ተጠቅመው ተጨባጭ ለዉጦችን   እያስመዘገቡ መሆናቸዉን  አስተያየታቸዉን ከሰጡት የመስኖ ተጠቃሚ አርሶ አደሮች መካከል  አቶ ዳኒኤል ሺፈታና  አቶ ኤልያስ ላጲሶ ተናግረዋል ።

አርሶ አደሮቹ ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ መደበኛ መስኖን ጨምሮ በዓመት 3 ጊዜ በማምረታቸዉ   ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸዉ እያጎለበተ መምጣቱና ከራሳቸው አልፎ ለቤተሰቦቻቸው ለአካባቢው ብሎም ለሀገራቸው እየደገፉ መሆነከን ተናግረዋል።

በወረዳዉ የሚገኙ ወጣቶችም   ጊዜያቸዉን  ከአልባሌ ቦታዎች ከማሳለፍ ተቆጥበዉ  መንግስት ባመቻቸላው  በተለያዩ የስራ ዘርፎች  በመሳተፍ የራሳቸዉንና የቤተሰባቸዉን  ህይወት ለመለወጥ ተጠናክረዉ መስራት እንዳለባቸዉም አስተያየት ሰጪዎቹ ገልፀዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *