የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የምግብ ዋስትና በአጭር ጊዜ ለማረጋገጥ ያስችላል ሲል የምስራቅ መስቃን ወረዳ ግብርና ፅ/ቤት ገለፀ።

የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የምግብ ዋስትናን በአጭር ጊዜ ለማረጋገጥና የዜጎችን ሕይወት ለማሻሻል እንደሚያስችል በጉራጌ ዞን የምስራቅ መስቃን ወረዳ ግብርና ፅ/ቤት ገለፀ።

የግብርና ፅ/ቤቱ ይህንን የገለፀው ከወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ጋር በመሆን በወረዳው እየተከናወነ ያለውን የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አሁን የደረሰበት ደረጃና እንዲሁም የውሃና የዩሪያ ቶፕ ድሬሲንግ እንቅስቃሴና ሌሎችም ያሉበት ደረጃን በጎበኙበት ወቅት ነው።

በአሁኑ ወቅት በወረዳው እየለማ የሚገኘው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የከርሰ ምድርና የገፀ ምድር የውሃ ሀብቶቻችንን ከሰው ኃይላችን ጋር በማቀናጀት በቀጣይ ልማቱን የማስፋፋት ስራም እንደሚሰራ የግብርና ፅ/ቤቱ አስታውቋል።

በወረዳው ከ142 ሄክታር በላይ መሬት በበጋ መስኖ በስንዴ እየለማ መሆኑም ከምስራቅ መስቃን ወረዳ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

በመረጃ ምንጭነት ገጻችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *