የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ስራው አበረታችና በጥሩ እድገት ላይ ይገኛል ሲል የበመስቃን ወረዳ ግብርና ልማት ፅ/ቤት ገለፀ።

የስንዴ ልማቱ አስመልክተው መረጃ የሰጡን የመስቃን ወረዳ የግብርና ጽ/ቤት ም/ሃላፊ እና የእርሻ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ጃቢር ጀማል እንዳሉት በ2014 አመተ ምህረት በግብርናው እንደ መንግስት ሰፊ ትኩረት ተሰቶ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል በዋነኝነት የሚጠቀሰው የዚህ የበጋ መስኖ የስንዴ ልማት መሆኑን ጠቅሰው በወረዳው በዚህ አመት 118 ሄክታር ለምቷል።

ከውጭ ተጽኖ ለመላቀቅና ከስንዴ ጠባቂ ላለመሆን ሁሉም የወረዳችን ባለድርሻ አካላት፣አርሶ አደሩ፣የጽፈት ቤቱ ባለሞያ ርብርብ በማድረግ የተሻለ ውጤት የተገኘበት ሁኔታ እንዳለ ማወቅ ተችሏል ብለዋል።

ይህ በቀጣይ ላሉት አመታት የተሻለ ለመስራት ጥሩ ልምድ የተወሰደበት ከመሆኑም በላይ አርሶ አደሩ ብዙ ትምህርት ወስዶ በዓመት ከሁለት ጊዜ በላይ ማልማት እንዲችል ማድረግ እና በስንዴ ልማት ዘርፍ አመርቂ ውጤት እንዲኖረው አስተዋጾኦ ይኖረዋል ብለዋል።

ከዚህ ውጪ የሚኖረው ከግብዓት አቅርቦ አኳያ እንደ ክልል እና ዞን ለወርዳችን እስከ 140 ኩንታል የስንዴ ዘር አቅርቦት እንዲሁም በዛው ትይዪ 140 ኩንታል NPS B ማዳበሪያ እና 140 ኩንታል ዩሪያ አቅርቦት ከመንግስት የተመቻቸ ሲሆን ካሁን በኋላም ላለው ስራ ድጋፉ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልጸዋል።

በዚህ ምክኒያት በቀበሌያችን የያዝነውን 220 ሄክታር የእርሻ መሬት የመጀመሪያው ዙር በ10 ቀበሌዎች ላይ እቅድ የያዝን ሲሆን በሂደት አርሶ አደሩ ላይ ተነሳሽነት በመፍጥር የቀበሊያችንን ቁጥር ከ 10 ወደ 12 በማሳደግ እና በዛው ልክ የመሬት ሽፋኑም የጨመረበት ሁኔታ መኖሩ ገልፀዋል።

አርሶ አደሩ ከመንግስት የቀረበለትን የስንዴ ዘር በተጨማሪም ከራሱ ሁለተኛ የዘር ምንጭ መጠቀሙ ገልፀው ልምዱም ሊበረታታ ይገባል ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ እንደ ተግዳሮት የምናየው ምናልባት በልማቱ ላይ የሚኖረው የተባይ እና በሽታን ለመከላከል አሁን ለአርሶ አደሮች እየተደረገ ያለው ድጋፍ እንዳለ ሆኖ አቅራቢያችን ካሉ ዩኒዬኖች እንደ ከዚህ ቀደም ያለንን ግንኙነት በማጠናከር መንግስትም በዚህ ጉዳይ ትኩረት ተሰቶት የተለያዩ የኬሚካል ውጤቶች ማግኘት ከተቻለ ምርትና ምርታማነቱ ላይ የራሱ የሆነ አዎንታዊ ተጽኖ ስለሚኖረው ጉዳት እንዳይደርስባቸው ማድረግ እንደሚቻል ገልፀዋል ሲል መረጃው ያደረሰን የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *