ከውጭ የሚገባው ስንዴ ለማስቀረት እንደ ሃገር የበጋ መስኖ ስንዴ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የገለጹት የምሁር አክሊል ወረዳ የግብርና ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ፈቀደ ክብሩ በወረዳው ካሉ ቀበሌዎች የተሻለ የውሃ አማራጭ ያላቸው ቀበሌዎች በመለየት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት እየለማ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
አክለውም የበጋ መስኖ ስንዴ ከሚለማበት ቦታ በዋናነት ውቅየ፣ ኤቸነ፣ቆረር፣ግናብ እንዲሁም ጨዛ ቀበሌዎች ሲሆኑ ልማቱ ውጤታማ እንዲሆን ጽ/ቤቱ ከሚመለከተው አካል ጋር በመተባበር በትጋት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
አክለውም ሀላፊው ስንዴው በበሽታና በተባይ እንዳይጠቃ የቅርብ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።
የበጋ መስኖ ስንዴ እያለሙ የሚገኙ ኣርሱ አደሮች ምርትና ምርታማነታቸው ለማሳደግ በወቅቱና በተገቢው ሁኔታ በተለይ የማዳበሪያ አጠቃቀም በማሻሻል ጊዜውን ጠብቆ ውሃ ማጠጣት እንደሚያስፈልግም ምክትል ኃላፊው አስታውቀዋል።
ከበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ስራ በተጨማሪ አርሶ ኣደሩ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ አጠናክሮ በመስራት የበልግ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንደሚያስፈልግ መግለፃቸው ከምሁር አክሊል ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በመረጃ ምንጭነት ገጻችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx