የበጋ መስኖ ስንዴ ለማምረት የተደረገው እርብርብ ውጤታማ መሆኑ በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ ግብርና ልማት ፅ/ቤት ገለፀ።

የወረዳው መንግሥትና ሌሎች የዘርፉ ባለሙያዎች ባደረጉት ድጋፍ የተሻለ ምርት ለመሰብሰብ መቃረባቸውን የመስኖ ተጠቃሚ የሆኑ የአቡኮና ጊቤ ቀበሌ አንዳንድ አርሶ አደሮች ገልጸዋል።

የወረዳው ምክትል አስዳዳሪና የግብርና ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ዘመተ አይፎክሩ እንደገለፁት የበጋ ስንዴን ለማምረት በወረዳው በተመረጡ አካባቢዎች በንቅናቄ የተጀመረ ሲሆን አሁን ያለበት ደረጃ በእጅጉ ተስፋ ሰጪ እንደሆነ በመስክ ምልከታ ለማረጋገጥ ተችሏል ።

የበጋ መስኖ ስንዴ ለማምረት አርሶ አደሩ፣አመራሩና የግብርናው ዘርፍ ባለሙያዎች ሀገራዊና ነባራዊ ሁኔታውን በመገንዘብ የምርት እጥረት እንዳያጋጥም በከፍተኛ ርብርብ ውጤት ለማምጣት ያደረጉት ትግል የሚደነቅ እንደሆነም ገልጿል።

የበጋ መስኖ ስንዴ በአካባቢያችን ለማስለመድ በርካታ ተግዳሮቶች የነበሩ ቢሆንም በአመራር ቁርጠኝነትና በባለሙያዎች ድጋፍ የተሻለ ምርት ለማግኘት በሚያስችል ደረጃ መድረሳቸውን በምልከታ ወቅት ተናግረዋል።

ተግዳሮቶችን በብቃት በመወጣት ዛሬ እያየን ያለነው ውጤት ላይ እንዲደርስ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ሁሉ ኃላፊ አቶ ዘመተ አይፎክሩ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

ሀገራችን በዚህ ወቅት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የበጋ መስኖ ስንዴ ወሳኝ ነው ያሉት አቶ ዘመተ አይፎክሩ የበጋ መስኖ ስንዴ ለማምረት የተደረገው ቁርጠኝነት በሌሎች በትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎችም መደገም አለበት ብለዋል።

አክለውም ሀላፊው ማንኛውንም አስቸጋሪ የሆኑ ተግባራትንም በተባበረ ክንድ ማከናወን እንደሚቻል የበጋ መስኖ ስንዴ ማሳያ ነው ማለታቸው ከወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በመረጃ ምንጭነት ገጻችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *