የቀድሞ የክልል ምክር ቤት አባላት ለዞኑ ህዝብ ተጠቃሚነት ስታደርጉት የነበረው ትግል አጠናክራችሁ ልትቀጥሉ ይገባል ሲሉ የጉራጌ ዞን ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ አርሽያ አህመድ አሳሰቡ።

የጉራጌ ዞን የ5ኛ ዙር የክልል ምክር ቤት አባላት ተመራጮች የሽኝት ፕሮግራም በዛሬው እለት በወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል።

የዞኑን ህዝብ ተጠቃሚ በሚያደርጉ ማንኛውም ጉዳዮች በያለንበት ቦታ የበኩላችንን እንወጣለን ሲሉ የቀድሞ የክልል ምክር ቤት አባላት ተናግሯል።

የጉራጌ ዞን ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ አርሽያ አህመድ በንግግራቸው ወቅት እንደገለፁት የሽኝት ስነ ስርአቱ ለየት የሚያደርገው በባለፋት አመታት ለወጡን ተከትሎ በምስራቅ መስቃንና በማረቆ ወረዳ የነበረው ግጭት ወደ ሰላም በተቀየረበት፣በእኖርና ኤነር ወረዳ በቆሴ ከተማ የነበረው የሰላምና ፀጥታ ችግር አንጻራዊ በሆነ መልኩ በተፈታበት እና ታላቁ የህዳሴ ግድባችን የመጀመርያው ሀይል ማመንጨት በጀመረበት ወቅት በመሆኑ ነው ብለዋል።

ላለፉት አምስት አመታት ህዝቡን በመወከል በክልል እና ለዞን ቋሚ ኮሚቴነት ተጨማሪ ኃላፈ በመውሰድ፣ በጉባኤ ወቅት በወቅቱ በመገኘት፣የወጡ ህጎችን በማስተግበር፣ እድገትና አንድነትን የሚያጠናክሩ ህጎች፣ ደንቦች፣ አዋጆች በማውጣት፣የክትትልና የቁጥጥር ስራ በመስራት በአጠቃላይ የምክር ቤቱ ተልእኮ እንዲሳካ እያደረጉት የነበረ ተግባር እጅግ ከፍተኛ እንደነበር ጠቅሰዋል።

በሀገራዊ ፈታኝ በሆኑ ጉዳዮች በህዳሴው ግድብ፣ በኮሮና ወረርሽ፣በስድስተኛ ዙር ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በተጨማሪም በጦርነቱ ወቅት ዞኑ በተሰጠው ተልእኮ በብቃት እንዲወጣ ሲያደርጉት የነበረው ጥረት የሚረሳ አይደለም ብለዋል።

ክብርት ወ/ሮ አርሺያ አህመድ አክለውም በምክር ቤቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትና ህዝቡን የበለጠ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራበት ገልጸዋል።

ለአብነትም የመስክ ምልከታዎች፣የህዝብ ለህዝብ የውይይት መድረኮች፣የፖናል ውይይቶች በአጠቃላይ በዞናችን ሳንጠቀምባቸው ያለፍንባቸው ጉዳዮች ላይ ከሌላ ጊዜው በተሻለ እንሰራበታለን ነው ያሉት።

ከዚህ በፊት ለዞኑ ህዝብ ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ሲያደርጉት የነበረው ተግባር በቀጣይም የዞናችን ህዝብ የሚጠይቃቸው የመሰረተ ልማት ስራዎችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት በሚደረገው ጥረት የሚያደርጉት እገዛ አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ክብርት ወ/ሮ አርሽያ አህመድ መልእክታቸውን አስተላልፏል።

የቀድሞ የክልል ምክር ቤት አባላት በሰጡት አስተያየት የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ለሌሎች ዞኖች አረያ የሆነ ምክር ቤት በመሆኑ ይህንን አቅሙ የበለጠ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ጠቁመዋል።

አክለውም የህዝብ ለህዝብ የውይይት መድረኮችና የወረዳ ምክር ቤቶች በማጠናከር እንዲሁም የሴቶችና ወጣቶች ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ መስራት እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

የዞኑ ህብረተሰብ በርካታ የሰላም፣የመሰረተ ልማት፣የመልካም አስተዳደር ጥያቄ አለው ያሉ ሲሆን በተለይም የህዝቡን አንድነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንዲሰጣቸው አሳስበዋል።

የዞኑን ህዝብ ተጠቃሚ በሚያደርጉ ማንኛውም ጉዳዮች በአለንበት ቦታ ሆነን የበኩላችንን እንወጣለን ሲሉ የቀድሞ የክልል ምክር ቤት አባላት ተናግሯል።

በመጨረሻም ለተሰናባች የክልል ምክር ቤት አባላት የእውቅና ሰርተፍኬት በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *