የቀቤኤንሲና ቋንቋን በማልማት የብሄረሰቡን ባህልና ታሪክን ጠብቆ ለማቆየት ያለዉ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ በጉራጌ ዞን የቀቤና ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት አስታወቀ።

ነሐሴ 27/2014 ዓ.ም

የቀቤኤንሲና ቋንቋን በማልማት የብሄረሰቡን ባህልና ታሪክን ጠብቆ ለማቆየት ያለዉ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ በጉራጌ ዞን የቀቤና ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት አስታወቀ።

በ2015 የትምህርት ዘመን በአዲሱ ፍኖተ ካርታ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋ መማር እንዲችሉ የመፅሀፍት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ፅ/ቤቱ ጠቁሟል።

የቀቤኤንሲና አፍ መፍቻ ቋንቋ ከ1989 ዓ.ም ጀምሮ በጉራጌ ዞን በቀቤና ወረዳና ከወረዳው ዉጪ ባሉት ትምህርት ቤቶች እየተሠጠ ይገኛል።

የቀቤና ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ ወይዘሪት ፋይዛ አለዊ እንደገለፁት ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋ በመማራቸዉ አካባቢያቸዉን በይበልጥ አዉቀዉ የማህበረሰቋንቋው፣ ባህልና ታሪክን ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና እንዳለዉ ገልፀዋል።

የቀቤኤንሲና ቋንቋ ለማሳደግ ፅ/ቤቱ ከወረዳዉ አስተዳደርና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ሀላፊዋ በመግለፅ በተለይም ዘንድሮ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት እንዲያገኙ ለማድረግ ከ200 ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ በ3 የትምህርት አይነቶች የመፅሀፍት ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

በተጠናቀቀዉ የትምህርት ዘመን በአዲሱ ፍኖተ ካርታ ተግባራዊ ለማድረግ በአንድ ትምህርት ቤት በሙከራ ደረጃ መስጠቱን በመጠቆም ዘንድሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልፀዋል።

ቋንቋዉ አሁን ካለበት ለማሳደግና ለትውልድ ተሻጋሪ እንዲሆን ከሳባን ወደ ላቲን ለመቀየር የዘርፉ ምሁራን ያሳተፈ ጥናት አየተካሄደ መሆኑን የበመግለፅ ስራዉ ተጠናቆ ወደ ተግባር እንዲገባ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል።

በቀጣይ ቋንቋው የበለጠ እንዲያድግ በኮሌጅና በዩኒቨርሲቲ ደረጃ በዘርፉ የሚያስተምሩ መምህራን የሚሠለጥኑበት ሁኔታ ለማመቻቸት እየተሰራ ይገኛልም ነው ያሉት።

በመፅሀፍት ዝግጅቱ ወቅት አግኝተን ካናጋገርናቸዉ ተሳታፊዎች መካከል አቶ ሙሰማ በደዊ፣ መምህር ጃፋር ሁሴን ፣ አለሀምዱ ሙዴና መምህርት ዘቢባ መኪዩ ይገኙበታል።

ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት አግኝተዉ የተሻለ ደረጃ መድረስ እንዲችሉ የመፅሐፍት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

ከዚህ ቀደም ከነበረዉ የመጽሐፍት ዝግጅት የአሁኑ ለተማሪዎች ምቹ ነዉ የሚሉት አዘጋጆቹ በተለይ በአፍ መፍቻ ቋንቋና በአከባቢዉ መምህራን መዘጋጀቱ ተማሪዎች ባህላቸዉንና ቋንቋቸዉን በተገቢው መልኩ አውቀው ለማሳደግ እድል እንደሚፈጥርላቸዉ ተናግረዋል።

መረጃው የወልቂጤ ኤፍ ኤም ነው።

እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Twitter:- https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *