የሺሻ ንግድ ቤቶችን በመቆጣጠር አምራችና ስራ ፈጣሪ ትዉልድን ለመፍጠር በሚደረገዉ ጥረት ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጋር በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ በጉራጌ ዞን የቀቤና ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት አስታወቀ።

ፅ/ቤቱ በወረዳዉ በተለያዩ አከባቢዎች ባደረገዉ ድንገተኛ ፍተሻ ከ150 በላይ የሺሻ እቃዎችን ሰብስቦ ማስወገዱን ጠቁሟል።

የቀቤና ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት የወንጀል መከላከል ሀላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ኑርሀሰን አስፋዉ በዚህ ወቅት እንዳሉት በወረዳዉ በተለያዩ አከባቢዎች የሺሻ ንግድና የመቃሚያ ቤቶች በመስፋፋታቸዉ ለተለያዩ ወንጀል ስራዎች መንስኤ እየሆኑ ይገኛል።

ወጣቱ ትዉልድ በአሁኑ ወቅት ከስራ ይልቅ ጊዜዉን በሺሻ ቤቶች ላይ ትኩረት አድርጎ መሰማራቱን ምክትል ኢንስፔክተሩ በመግለፅ ህገ ወጥ ንግዱን ለመከላከል የፖሊስ አባላቱ ከምንም ጊዜ በላይ እየሰራ ይገኛልም ብለዋል።

የወረዳዉ ምክር ቤት በ2012 ዓም ህገ ወጥ ንግዱን በማዉገዝ ህጋዊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ባፀደቀዉ መሰረት በሺሻ ነጋዴዎች ላይ የእስራትና የገንዘብ ቅጣት መቀጣቱን በማስታወስ አስተዳደር እርምጃ የመውሰዱ ስራ ተጣክሮ ይቀጥላሉ ብለዋል።

በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ ከ150 በላይ የሺሻ እቃዎችን ሰብስቦ ማስወገዱ ገልፀዉ ህብረተሰቡም ከፖሊስ ጋር በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ አመላክተዋል።

የሺሻ እቃዎችን ሲያስወግዱ አግኝተን ካነጋገርናቸዉ ነዋሪዎች መካከል ሀጂ በድሩ ሁሴን፡ ሀሰን ናስር ፈቲሃ ግርማና ህያር ሀሰን ይገኙበታል።

የሺሻ ቤቶች ትዉልድን እየገደለ መሆኑን በመግለፅ ድርጊቱ በህግም ሆነ በባህልና በሀይማኖት የሚወገዝ እንደሆነ ገልፀዋል።

በመሆኑም የተሻለ ትዉልድን ለመፍጠር የሺሻ ንግድ ቤቶችን ለመቆጣጠር በሚደረገው እንቅስቃሴ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራ ሊሰራ ይገባልም ብለዋል አስተያየት ሰጪዎቹ።

ዘጋቢ፦ ሪያድ ሙህዲን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *