ተፈናቃዮች ለመደገፍ ያለመ የገቢ ማስገኛ እና የውጭ ጣልቃ ገብነት ለመቃወም የተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች በቡኢ ከተማ ተካሄደ። በዚህም ከ 200 ሺህ ብር በላይ በዛሬው እለት ብቻ መሰብሰብ መቻሉን ተጠቁሟል።
የሶዶ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሴ አበጋዝና የቡኢ ከተማ ከንቲባ አቶ ይሽልጌታ እንደተናገሩት በሀገሪቱ የተከፈተው የውጭና የውስጥ ጦርነት ለመመከት የከተማው እና የወረዳው ነዋሪዎች የስንቅና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ደጀንነታቸውን አሳይተዋል።
አሸባሪው የህወሓት ቡድን በከፈተው ጦርነትን ከፍተኛ ከጥር ያላው ህዝብ ከቀየው መፈናቀሉን ተከትሎ በሀገሪቱ የሚፈጠረው ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመመከት በግብርናውና በኢንዱስትሪው ዘርፍ ተጨባጭ ውጤት ለማስመዝገብ በትኩረት ይሰራል ብለዋል አስተዳሰሪዎቹ።
አያይዘውም አስተዳዳሪዎቹ የቡኢ ከተማ እና የሶዶ ወረዳ አስተዳደሮች በመቀናጀት በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ወገኖች መልሶ ለማቋቋም የሚያግዝ ገቢ ለመሰብሰብ የአትሌቲክስ እና የእግርኳስ ውድድር በየኢ ከተማ ተዘጋጅቷል። በዚህ ውድድር ከስቴዲየም መግቢያና የምዕራባውያን ጣልቃገብነት ከሚያወግዝ #በቃ #NOMORE ቲሸርት ሽያጭና ከሁለት መቶ የህ ወር በላይ ገቢ መሰብሰብ እንደተቻለ አስረድተዋል።
የስፖርታዊ ውድድሩ አስተባባሪ አቶ እንዳለ ንጉሴ በሰጡት አስተያየት ስፖርታዊ ውድድሩ ሀገሪቱ በገጠማት የህልውና ጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ በማድረግ አጋርነታቸውን ለመግልጽ እንደሆነ አስረድተዋል። ይህን ተግባር ውጤታማ ለማድረግ መንግስታዊ ተቋማት፣ ባንኮችና ሌሎች አጋር ድርጅቶች እንደተሳተፉ አቶ እንዳለ ንጉሴ ገልጸዋል።
አቶ ዝናቡ ካሱ ወይዘሮ ርስት ረዲኤት የቡኢ ከተማ ነዋሪ ናቸው። ነዋሪዎቹ በአፋርና በአማራ ክልሎች ለተፈናቀሉ ወገኖች በተለያዩ የገቢ ማስገኛ ስራዎች በመሰማራት አለኝታነታቸውን አሳይተዋል።
በሩጫው ከመሳተፍ በተጨማሪ ቲሸርት በመግዛት በንቃት ሲሳተፉ እንደነበር ነዋሪዎቹ አስረድተዋል ።
ውድድሩ በቡኢ ከተማ የትሚኖ የጤና ቡድን አባላት መነሻነት መጀመሩን የገለፁት ነዋሪዎቹ ከወረዳውና ከተማ አመራሮች ጋር በመቀናጀት ውጤታማ ስራ መስራት እንደተቻለ አስረድተዋል።
በመጨረሻም የቡኢ ከተማ የትሚኖት የጤና ቡድንም ከቡታጅራው አንድነት የጤና ቡድንም ጋር ባደረጉት የእግርኳስ ውድድር ፕሮግራሙ ተጠናቋል።