የስፖርት ዘርፉ የህብረተሰቡ ጤና የምናስጠብቅበትና ወንድማማችነትን የምናጠናክርበት ማድረግ እንደሚያስፈልግ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል ገለጹ

ጥቅምት 4/2015 ዓ/ም
የስፖርት ዘርፉ የህብረተሰቡ ጤና የምናስጠብቅበትና ወንድማማችነትን የምናጠናክርበት ማድረግ እንደሚያስፈልግ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል ገለጹ

ይህን የተባለው የጉራጌ ዞን የስፖርት ምክር ቤት 20ኛ ዙር ጠቅላላ ጉባኤው በቆሼ ከተማ ባካሄደበት ወቅት ነው።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል እንዳሉት የስፖርት ዘርፋ ለኢኮኖሚ እድገትና የህዝቡ አንድነትን የበለጠ ለማጠናከር ጉልህ ሚና ይጫወታል።

በመሆኑም የስፖርት ልማት ዘርፉን ለማሳደግ በትምህርት ቤቶች፣ በታዳጊ ፕሮጀክቶች፣ ከዩኒቨርስቲና ከግል ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

የስፖርት ሀብት ልማቱ ለማሳደግ ቅድሚያ አሳታፊ መሆን ያስፈልጋል ያሉት አቶ መሀመድ የዞኑ የስፖርት አቅም አሟጦ በመጠቀም ህብረተሰቡ በስፖርቱ ተጠቃሚ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።

የስፖርት ዘርፉ የህብረተሰቡ ጤና የምናስጠብቅበትና ወንድማማችነትን የምናጠናክርበት ማድረግ እንደሚያስፈል አስታዉቀው የስፖርት ማዘውተርያ ስፍራዎች መበራከት እንዳለባቸውና ያሉትንም ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዲኖራቸው ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አወል ጅማቶ እንደገለጹት በቀጣይ ከዚህ በፊት የነበሩ ክፍቶች በማረም እንዲሁም የፕሮጀክትና የክለብ ውድድሮች እንደሚካሄዱ አስታውቀዋል።

በአመቱ በተደረጉ ውድድሮች አበረታች ውጤት ተመዝግቧል ያሉት ኃላፊው የስፖርቱ ዘርፉ በስነ ምግባርና በስፖርት የታነጸ ትውልድ ለማፍራት ብሎም የህዝቡ አንድነትን እንዲያጠናክር በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቋል።

የመምሪያው ምክትልና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አደም ሽኩር እንደገለጹት በ19ኛው የክልል የባህል ስፖርቶች ውድድር ላይ እንደ ዞን በ11 ስፖርት ዓይነት መሣተፍ መቻሉ ተናግሯል።

በነዚህም በአትሌቲክስ ወንድ 1ኛ፣ በአትሌቲክስ ሴት 1ኛ እና በቅ/ኳስ ወንድ 1ኛ፣ በባህል ስፖርት በገበጣ 12 ወንድ 1ኛ፣ በሻህ ወንድ 1ኛ፣ በቡብ ሴት 1ኛ በፓራሎምፒክስ 2ኛ፣ በጠረጴዛ ቴኒስ 2ኛ እና በ3 የውድድር መደብ 3 ዋንጫ፣ በጠረጴዛ ቴኒስ ስፖርት 1 የፀባይ ዋንጫ፣ በውሹ 1 የፀባይ ዋንጫ፣ በብስክሌት 2ኛ ደረጃ መውጣት ተችሏል ነው ያሉት።

በአጠቃላይ 32 የወርቅ ፣ 24 የብር እና 25 የነሀስ በድምሩ 81 ሜዳሊያዎች እና 15 ዋንጫዎች በአጠቃላይ ድምር ውጤት እና በተሳትፎ በክልሉ 3ኛ ደረጃ በመውጣት በስኬት ማጠናቀቅ ተችሏል ብለዋል፡፡

ተተኪ ስፖርተኞችን ለማሳደግና ለማሰልጠን በ13 የፕሮጀክት ጣቢያዎች አቅምን በአገናዘበ ስፖርቶች በእግር ኳስ፣ በአትሌቲክስ፣ በቅርጫት ኳስ፣ በእጅ ኳስ፣ በወርልድ ቴኳንዶ ፣ጠረጴዛ ቴኒስ፣ብሰክሌት እና በፓራ ኦሎምፒክስ የስፖርት ዓይነቶች ቡታጀራ፣ ወልቂጤ፣ ሶዶ፣ እዣ፣ ቸሃ፣ ቀቤና እና አበሽጌ ባሉ መዋቅሮች መከፈቱ ጠቁመዋል ፡፡

በጠቅላላ በአመቱ በስፖርቱ ዘርፍ 4ሚሊየን 81 ሺህ 19 ብር ገቢ መሰብሰቡና 3 ሚሊየን 2 መቶ 97 ሺህ 344 ለተለያዩ ስራዎች ወጪ መደረጉን ለስፓርት ምክር ቤት አቅርበዋል።

በዞኑ ለሚገኙ የስፖርት ክለቦች በበጀት ዓመቱ 9 ሚሊየን 7መቶ ሺህ ብር በማሰባሰብ ለወልቂጤ ከተማ እግርኳስ ክለብ ፤ለወልቂጤ ከተማ ቅርጫት ኳስ ክለብ ፤ለዘቢዳር አትሌቲክስ ክለብ እና ለቡታጅራ እግር ኳስ ክለብ እና የስፖርት ምክር ቤት የዞን አስተዳደር ድጎማ መደረጉ አቶ አደም ተናግሯል።

በዞናችን ውስጥ በጤናና በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስፖርት በመኖሪያ ቦታዎች በትምህርት ቤቶችና በመስሪያ ቦታዎች 40ሺ 6መቶ12 የህብረተሰብ ክፍሎችን ተሳታፊና ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ ኃላፊው አስታውቋል።

በጉባኤው የተሳተፉ አካላት እንዳሉት ዞኑ ለስፖርት ስራው አመቺ እንደመሆኑ መጠን ቀጣይ ብዙ መስራት እንደሚጠበቅ አንስተዋል።

የስፖርት ዘርፉን ለማጠናከር በስፖርት ስም የሚሰበሰቡ ገንዞቦች በወቅቱ ገቢ በማድረግ፣ የተቀዛቀዙ የስፖርት ውድድሮችን በማነቃቃት፣ የስፖርት ማዘውተርያ ቦታዎችን በማስፋት፣ ታዳጊ የስፖርት ክለቦችን በመደገፍና በማስጀመር ስራዎች መስራት ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን የህብረተሰቡ ጤና እንዲጠበቅ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ነው ያሉት።

በጉባኤውም የ2015 የስፖርት ምክርቤት እቅድና የስፖርት ምክር ቤቱ ገቢ አሰባሰብ መመሪያ ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በስፖርቱ ዘርፍ ዞኑን ያስጠሩና አመረቂ ውጤት እያስመዘገቡ ያሉ ወጣቶች የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።
ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Tiwter https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *