የስርዓተ ምግብ ማሻሻያና ማጠናከሪያ ፕሮግራም(FSRP) በወረዳው ውስጥ በርካታ የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት በማከናወን ትልቅ ውለታ መዋሉን ተገለጸ።
በ2016 ዓ.ም በFSRP ፕሮጀክት በተሰሩ ስራዎች አፈጻጸምና በ2017 ዓ.ም እቅድ አተገባበርና ውጤታማነት ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ።
የምክክር ሰነዱን ያቀረቡት በወረዳው የፕሮጀክቱ እስተባባሪ አቶ ጌቱ ኮራ ፕሮግራሙ በወረዳው በግብርና ስራዎች፣ በቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ የግንዛቤ ስልጠና በመስጠት፣ውሃ ማጠራቀሚያ ኩሬዎችን በመቆፈር፣የገበሬዎች ልምድ ልውውጥ በማድረግ፣በሴቶችና በወጣቶች ተጠቃሚነት፣በስራ እድል ፈጠራ፣በእንስሳት ጤና፣በመስኖ ስራ፣በስርዓተ ምግብ ማሻሻያ፣የኑሮ ውድነት በመቀነስና በሌሎችም ዘርፎች ላይ በርካታ ስራዎችን መስራት መቻሉን አብራርተዋል።
አቶ ጌቱ ገለጻ እንዳጠቃላይ FSRP ፕሮግራም በወረዳው በሁሉም ዘርፎች የአቅም ግንባታ ስራዎችን እየሰራ መሆኑንም አመላክተዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ እንደገለጹት የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ መሆን እንደ እድል በመውሰድ ከፕሮግራሙ አሰራርና ደንብ በማይጋጭ መንገድ ስራዎችን ለህዝብ ተጠቃሚነት መስራት ይገባልም ብለዋል።
አቶ አበራ አክለውም ፕሮጀክቱ ከመንግስት ጎን በመቆም ያሉ ጉለቶችን የሚያሟላ በመሆኑ በተገቢው መምራትና መጠቀም እንደሚገባም አሳስበዋል።
ወረዳው ይህን አጋጣሚ በተገቢው በመጠቀም ተጨማሪ ሀብት ለመፍጠር መስራት ይገባልም ነው ያሉት።
እንደ ኃላፊው ገለጻ በፕሮጀክቱ የተፈጠሩ ሀብቶች ዘመን ተሻጋሪና ቀጣይነት እንዲኖራቸው የሁሉም አመራሩና ሌሎችም ባለድርሻ ተቋማት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል።
በመድረኩ የተገኙት የወረዳው የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ሞሸዲን አህመድ እንደገለጹት ፕሮጀክቱ የወረዳው የግብርና እንዲሁም ሌሎችም የመንግስት ስራዎች አንድ እርምጃ ከፍ እያደረገ እንደሆነ ተናግረዋል።
አቶ ሞሸዲን አክለውም ከፕሮግራሙ ጋር እየሰሩ ያሉ ባለድርሻ ተቋማት የህዝብ ተጠቃሚነት ላይ በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባም አመላክተዋል።
የቀድሞ ኤጂፒ(AGP) የአሁኑ የስርዓተ ምግብ ማሻሻያና ማጠናከሪያ ፕሮግራም(FSRP) በወረዳው ውስጥ በርካታ የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት በማከናወን ትልቅ ውለታ የዋለ ፕሮግራም መሆኑን አውስቷል።
ፕሮጀክቱ ለወረዳው ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ በመሆኑ አመራሩ በተገቢው በማገዝ
የህዝቡ ተጠቃሚነት ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ የመንግስት ዋና ተጠሪው አመላክተዋል።
የወረዳው የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብድልመጂድ ጀማል በበኩላቸው ፕሮግራሙ ለግብርናው ዘርፍ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም እንደ ወረዳ ከፕሮጀክቱ ጋር በተሰራው ቅንጅታዊ ስራ በግብርናው ምርትና ምርታማነት ላይ አመርቂ ለወጥ መመዝገቡንም አስረድቷል።
በመድረኩ የተገኙ ባለድርሻ አካላት በሰጡት አስተያየት ፕሮጀክቱ በወረዳው በሁሉም ዘርፍ በሚባል መልኩ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም አጋጣሚውን በመጠቀም የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ በመድረኩ ተመላክቷል።
በመድረኩ የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ አበራ ወንድሙ፣የወረዳው የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ሞሸዲን አህመድ፣የወረዳው አመራሮችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ዘገባው የወረዳው መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው