የሴቶች የኢኮኖሚ አቅም ለማሳደግ በመኸር ወቅት የታዩ አበረታች ስራዎችን በመስኖ ወቅትም አጠናክሮ ማስቀጠል እንደ ሚገባ የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህጻናት መምሪያ አስታወቀ።

በ2013 አመተ ምህረት በዞኑ በሴቶች በመኸር ስራ ይለማል ተብሎ ከታቀደው 3መቶ ሄክታር መሬት ሙሉ ለሙሉ መልማቱ ተገልጿል።

የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህጻናት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ መሰረት አመርጋ እንዳሉት የዞኑ ሴቶች የኢኮኖሚ አቅማቸው ለማሳደግ በመኸር ፤በበልግ እና በመስኖ ወቅቶች በከብቶች በድለባ፣በዶሮ እርባታ፣ በገብስና በስንዴ ምርት፣ በድንች፣ በጓሮ አትክልቶችና በሌሎችም የስራ ዘርፎችም እየተሳተፉ እንደሆነ ገልጸዋል።

ሴቶቹ ዘመናዊ የአስተራረስ ዘዴ እንዲከተሉ ከፌደራልና ከክልል የሚመለከታቸው አጋር ድርጀቶችና ተቋሟት ጋር በመሆን የቁሳቁስ እና የተለያዩ ግብአቶች በሽልማት እንዲሁም በድጋፍ ተበርክቶላቸዋል ነው ያሉት።
ከዚህ በፊት ሴቶቹ በቆጠቡት ቁጠባ እስከ 7መቶ ሚሊየን ብር መቆጠብ የቻሉ እንደነበር ያስታወሱት ወ/ሮ መሰረት አመርጋ ይህንን የቁጠባ ልምዳቸውን ለማሳደግም በህብረት ስራ ማህበር፣በዩኒየኖች፣ በኦሞ ፣በባንክ እና በባህላዊ መንገዶች እየቆጠቡ እንደሆነ ተናግሯል።
ደቡብ ሶዶ ፣ቸሀ ፣መስቃን፣ አበሽጌ ፣ጉመር እና እንደጋኝ ለአብነት ጥሩ አፈጻጸም ያላቸው ሲሆኑ ስራው ግን በሁለም ወረዳዎች ተጠናክሮ እየቀጠለ ይገኛል ብለዋል።

የሚያመርቱበት ቦታ ምቹ እንዲሆን በማድረግ፣ የምርጥ ዘር እጥረት እንዳይገጥማቸው በማድረግ ፣የተበላሹ ሞተር ፓምፖች የማስጠገን፣ የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸው መሰራቱን ገልፀው የሴቶቹ ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ሚመለከተው ሁሉ የድርሻውን መወጣት ያስፈልጋል ብለዋል።

በዘንድሮ አመት በመስኖ ወቅት 14ሺ 755 ሄክታር መሬት በሴቶች ልማት ቡድን ለማልመት ታቅዶ የንቅናቄ ስራ ተሰርቶ ወደተግባር መገባቱን የገለፁት ኃላፊዋ ሀገራችን አሁን የገጠማት የውጭ ጫናና የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ ሴቶችን በማደራጀች በመኸር ወቅት የታዩ አበረታች ስራዎችን በመስኖ ወቅትም አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።
የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህጻናት መምሪያ የሴቶች ንቅናቄ ስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ባጋሮ ኮርታዊ እንደገለፁት በዞኑ 7ሺ138 የልማት ቡድኖች የሚገኙ ሲሆን 2መቶ 31ሺ 728 አባላት መኖራቸው አሳውቀዋል።

በዚህም በ2013 አመተ ምህረት በዞኑ በሴቶች በመኸር ወቅት ይለማል ተብሎ ከታቀደው 3መቶ ሄክታር መሬት ሙሉ ለሙሉ መልማቱ ገልፀው ለስራው ውጤታማነት አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ እንደነበር አመላክቷል።

በዚህም በየጊዜው በሚደረገው እንቅስቃሴ የሴቶች የኢኮኖሚ አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ በፖለቲካ እንዲሁም በማህበራዊ ኑሮዋቸው ላይ ለውጥ እያመጡ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ወ/ሮ ዘይነባ አወል በቸሀ ወረዳ ፣ ወ/ሮ ወሄወት ማሬ በጉመር ወረዳ ፣ወ/ሮ አስካለ ወ/ማርያም በእዣ ወረዳ በማህበር ተደራጅተው የሚሰሩ ሴቶች ናቸው። እንደነርሱ ገለፃ ቀደም ሲል ምንም የገንዘብ ምንጭ ባለመኖሩ ይቸገሩና ከባሎቻቸው እርዳታ ይፈልጉ እንደነበር አስታውሰው ከተደራጁ በኋላ ግን በማህበራቸው እና በግላቸው የተቸገሩ ወገኖችን መርዳት መጀመራቸው አሳውቀዋል።

የኑሮ ውድነት የምናሸንፈው በግብርና በመሆኑ ሴቶች የባሎቻቸውን እጅ ከማየት ወጥተው ተደራጅተው በመስራት ኑሮአቸውንንማሻሻል እንዳለባቸውና ልጆቻቸውን ያለ ጭንቀት እንዲማሩ ማስቻል እንዳለባቸው ተናግዋል።

በሴቶች የልማት ቡድን ተገናኝተው የቁጠባ ባህላቸውን ከማሳደጋቸው ባለፈ የግብርና ስራቸው ውጤታማ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል።
ስለሴቶች ጉዳይ፣ ስለጎጂ ባህላዊ ድርጊቶች እና ስለ ጤና አጠባበቅ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ መግለፃቸው የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *