የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች መምሪያ የ2016 ዓመተ ምህረት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2017 ዓመተ ምህረት የግብ ስምምነት መድረክ በወልቂጤ ከተማ አካሄዷል።
በመድረኩ የተገኙት የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ረዳት የመንግስት ተጠሪና የፖለቲካና ርዕዮተ አለም ዘርፍ ሀላፊ አቶ ናስር ሀሰን እንዳሉት የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ባለዉ ስራ ለዉጥ እየመጣ እንደሆነም አመላክተዉ በቀጣይም ሴቶች በሁሉም ዘርፎች ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ የግንዛቤዉ ስራ በስፋት መሰራት እንዳለበትም ተናግረዋል።
በዘርፉ ሰዉ ተኮር ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን ይህንንም የበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል።
ሴቶች በተሰማሩበት ዘርፍ ዉጤታማ ስራ እየሰሩ እንደሆነም ጠቁመዉ በዘርፉ የተሻለ ለዉጥ እንዲመጣ የቅንጅት ስራዉ የበለጠ ማጠናከር እንደሚገባም አስረድተዋል።
የሴቶችና ህጻናት ስራዎች ከሁሉም ተቋማቶች ጋር በመቀናጀት የሚሰራ እንደሆነም ያመላከቱት አቶ ናስር በዘርፉ የተሻለ ዉጤት እንዲመጣ ከመቼዉም ጊዜ በላይ አጽኖት ተሰጥቶት መሰራት እንዳለበትም አብራርተዋል።
ያሉ ጉድለቶችን ነቅሶ በማዉጣት በተያዘዉ ጀት አመት የሴቶችና ህጻናት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባም አስረድተዋል።
የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች መምሪያ ሀላፊ ወይዘሮ ነጅብያ መሀመድ በበኩላቸዉ ሴቶች ወደ መሪነትና ዉሳኔ ሰጪነት ላይ ተሳትፎአቸዉ ከፍ እንዲል የሁሉም እገዛና ትኩረት ይሻል ብለዋል።
በሴቶች ህብረት አደረጃጀት በበጀት አመቱ 209 ሚሊየን 80 ሺህ 466 ብር ለመቆጠብ ታቅዶ በዚህም በ190 ሺህ 201 ሴቶች 211 ሚሊየን 4 መቶ 60 ሺህ 958 ብር መቆጠብ እንደተቻለም አስረድተዋል።
ከብድር አሰጣጥ አንጻር 84 ሚሊየን 100 ሺህ 877 ብር ብድር ለማመቻቸት ታቅዶ ለ88 ሺህ 177 ሴቶች 87 ሚሊየን 183 ሺህ 701 ብር ብድር ማግኘት እንደቻሉም ጠቁመዋል።
የተለያዩ ማህበራዊና አስተዳደራዊ በደልና ጥቃት የደረሰባቸዉ 1ሺህ 3 መቶ 78 ሴቶችና 243 ህጻናት የህግ ድጋፍና አገልግሎት መስጠት ተችሏል ብለዋል።
በሁሉም መዋቅሮች 16 የህጻናት ፓርላማ ማቋቋም ተችሏል ብለዉ 555 ሴቶች 107 ህጻናት ጉዳያቸዉ በፍርድ ቤት የመከታተል ስራ መሰራቱም ተናግረዋል።
በማህበረሰብ አቀፍ አደረጃጀቶችና ከመንግስታዊ አካላት በመቀናጀትና በማስተባበር በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ዉስጥ ላሉ 20 ሺህ 620 ህጻናት ድጋፍና እንክብካቤ ማድረግ እንደተቻለና ሌሎችም በርካታ ስራዎች በቅንጅት መስራት እንደተቻለም አመላክተዋል።
በተያዘዉ በጀት አመት የሴቶችና ህጻናት ተሳትፎና ተጠቃሚነት ላይ የበለጠ ዉጤታማ ስራ ለመስራት ቅንጅታዊዉ ስራዉ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
በመድረኩ የተገኙ አንዳንድ ባለ ድርሻ አካላቶች በሰጡት አስተያየት የሴቶችና ህጻናት ተሳትፎና ተጠቃሚነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ያለዉን ስራ የሚበረታታ እንደሆነም አስረድተዉ በተያዘዉ በጀት አመት በእቅድ የተያዙ ግቦች ስኬታማ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰሩም ተናግረዋል።
በመጨረሻም በ2016 ዓመተ ምህረት በወረዳዎች ደረጃ 1ኛ
የቸሃ ወረዳ 2ኛ የእኖር ወረዳ ፣ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳና የእዣ ወረዳ ሴቶችና ህጻናት ጽህፈት ቤቶች በተመሳሳይ ዉጤት 3ኛ ደረጃ በማግኘት የሰርተፍኬትና የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በከተማ መዋቅሮች ደረጃ 1ኛ የእምድብር ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህጻናት ጽህፈት ቤት ፣ 2ኛ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህጻናት ጽህፈት ቤት ፣ 3ኛ የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህጻናት ጽህፈት ቤቶች የዋንጫና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።
ለአጋር መምሪያዎች ማለትም ለግብርና መምሪያ ፣ፍትህ መምሪያና ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን እንዲሁም የዞኑ ዉሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያዎች እንዲሁም የዞኑ ሴቶችና ህጻናት ተቋም የተሻለ አፈጻጸም ያላቸዉ ባለሙያተኞች የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል
መምሪያዉ ከሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የ2017 የግብ ስምነት ተፈራርመዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ ነዉ።