የሴቶች ልማት ቡድን መጠናከር በሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ እድገት ላይ የሚያስገኘው ለውጥ ከፍተኛ በመሆኑ ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ሴቶች እና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ አስታወቀ።

መምሪያው የአምስት ወራት እቅድ አፈፃፀም በወልቂጤ ከተማ ዛሬ ገምግሟል ።

የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ መሠረት አመርጋ እንደተናገሩት እንደሀገር የገጠመንን ችግር ለመመከት በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ሴቶች እያሳዩ ያለው አጋርነት ከፍተኛ ነው።

ሴቶች በኢኮኖሚ ሲበለፅጉ ሀገር ትበለፅጋለች ያሉት ወይዘሮ መሠረት በዞኑ ውስጥ በማህበረሰብ አቀፍ ድጋፍና እንክብካቤ ሴቶች የማይተካ ሚና እየተጫወቱ መሆናቸው አብራርተዋልው
በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በማስወገድ በአንፃሩ የሴቷን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መሰራት እንዳለበት ኃላፊዋ አክለው ገልጸዋል።

በመድረኩ የተመረጡ ወረዳዎች ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን የመድረኩ ተሳታፊዎች ባለፉት አምስት ወራት የተከናወኑ ተግባራት አበረታች እንደነበሩ የሚያያሳዩ ናቸው ብለዋል፡፡

ተሳታፊዎቹ በድክመት ካነሷቸው ተግባራት መካከል ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት እና የሴቶች ልማት ቡድን አለመጠናከር ሲሆኑ በቀጣይ ለተግባራቱ ልዩ ትኩረት በመስጠት ውጤታማ ተግባራት ማከናወን እንደሚቻል ገልፀዋል፡፡

የሴቶች ልማት ቡድን መጠናከር በሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ እድገት ላይ የሚያስገኘው ለውጥ ከፍተኛ በመሆኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅተው እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

አያይዘውም ተሳታፊዎቹ ሴቶች የልማት ቡድኖቻቸው በማጠናከር የቁጠባ ባህላቸው ይበልጥ እንዲያጎለብቱ መስራት ይገባል ብለዋል ሲል የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዘግቧል፡፡

= አካባቢህን ጠብቅ!
= ወደ ግንባር ዝመት!
= መከላከያን ደግፍ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡

Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *