የሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት ለማረጋገጥ የዞን ምክር ቤት ሴት ተመራጮች የኮከስ አባላት አቅም ማጎልበት እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ምክርቤት አስታወቀ።

ምክር ቤቱ ከዞኑ ሴቶችና ህጻናት መምሪያ ጋር በመቀናጀት በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ለመከላከል የሚያስችል ስልጠና ለኮከስ አባላት ሰጥተዋል ።

የዞኑ ሴት የምክርቤት ተመራጮች ኮከስ የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም በወልቂጤ ከተማ መገምገሙን ተመልክቷል ።

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ክብርት ወይዘሮ አርሺያ አህመድ እንደተናገሩት ሴቶች በማህበራዊ፣ በፖለቲካዊና በኢኮኖሚ ያላቸውን ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የሴቶች ኮከስ ማጠናከር ይገባል።

የኮከሱ መጠናከር ዘርፈ ብዙዎች ጠቀሜታ እንዳለው የተናገሩት ክብርት አፈጉባኤዋ በተለያዩ ምክንያቶች ቤት ውስጥ የቀሩ አቅም ያላቸው ሴቶች ወደ መድረክ እንዲወጡ በማድረግ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል ብለዋል።

ሴቶች በህግ አውጪ ደረጃ ያላቸው ተሳትፎ የተሻለ ቢሆንም በህግ አስፈጻሚና ተርጓሚ ደረጃ ላይ ያላቸው ዝቅተኛ ተሳትፎ ለማሻሻል ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ሴት አመራሮች በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ዋና አፈጉባኤዋ አስገንዝበዋል።

ኮከሱ ጠንካራ አባላት ለማፍራትና የሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ በመሆኑ የራሱ የገቢ ምንጭ የኖረው ይገባል።

በአሁን ወቅት ኮከሱ የራሱ የሆነ የገቢ ምንጭ የሌለው በመሆኑ ምክርቤት ከተበጀተለት በጀት ቀንሶ እንደሚደግፈው የገለጹት ክብርት ወይዘሮ አርሺያ የኮከሱ ውጤታማነት ለማረጋገጥ እና የራሱ የገቢ ምንጭ እንዲኖረው ማናቸውም የኮከሱ አባላት የሙያ፣ የቁሳቁስና የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

የኮከሱ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት ወይዘሮ አየለች በበኩላቸው ኮከሱ ከተቋቋመ ወዲህ የሴቶች ተሳትፎ እያደገ መጥቷል ብለዋል።

እንደ ወይዘሮ አየለች ገለፃ የኮከሰ አባላት የመንግስት ተቋማት ተልዕኮ በመረዳት አፈጻጸማቸውን የመገምገም አቅም እንዲያጎለብቱ አስችሏቸዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ሪፖርቱ ክፍተቶቻቸው በመሙላት በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት መነሳሳትን እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም ለኮከስ ሲሰጠው የነበረው ትኩረት አናሳ በመሆኑ ውጤታማ እንዳልነበረ የገለፁት ተሳታፊዎቹ አሁን ትኩረት አግኝቶ እራሱን አስችሎ እቅዱን መገምገሙ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ይረዳል ብለዋል።

አክለውም ተሳታፊዎቹ ሴቶች በማህበራዊ ዘርፍ በሚያደርጉት ንቁ ተሳትፎ በትምህርት፣ በእናቶችና ህጻናት ደህንነት፣ በግልና አካባቢ ንጽህናና በሌሎች ተግባራት የላቀ ውጤት ማስመዝገብ እንደቻሉ አብራርተዋል።

በሌላ በኩል ሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውና ፖለቲካዊ ተሳትፏቸው አነስተኛ በመሆኑ በቀጣይ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

በጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ስልጠና የሰጡት የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህጻናት መምሪያ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ሀሊማ ለጋ በዞኑ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ለመከላከል የኮከሰ አባላት ጉልህ ሚና መጫወት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

በበጀት አመቱ በሴቶችና ህጻናት ላይ የአስገድዶ መድፈር፣ ጠለፋ፣ ድብደባና የግድያ ድርጊቶች ተፈጽሞባቸዋል።

እነዚህ ድርጊቶች የፈጸሙ ግለሰቦች በህግ እንዲጠየቁ እና መሰል ድርጊቶች ዳግም እንዳይፈጸምባቸው ለመከላከል አደረጃጀቶችን ከማጠናከር በተጨማሪ የፍትህ አካላት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት እንዲሰጡ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

የመምሪያው ኃላፊ ወይዘሮ መሰረት አመርጋ በበኩላቸው ሴቶች በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸው ተሳትፎ ከፍተኛ እንደሆነ አስረድተዋል።ይሁን እንጁ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች አሳዛኝና ልብ ስባሪ በመሆናቸው ሁሉም ሊያወግዘው ይገባል ብለዋል።

እንደ ኃላፊዋ ገለጻ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ እንደ ጠለፋ፣ አስገድዶ መድፈር፣ግድያ፣ግርዛት እና የመሳሰሉት ድርጊቶች ወቅቱን የማይመጥኑ በመሆናቸው በዘላቂነት ለማስቆም ምክርቤቶች፣የሀይማኖት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎች፣ አጋር ድርጅቶች፣ የፍትህ ተቋማት እና ሌሎች አደረጃጀቶች ርብርብ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

=ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *