የሴቶች ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የዞን ምክር ቤት የሴት ተመራጮች ህብረት ወይም የኮከስ አባላት አቅም ማጎልበት እንደሚገባና ውጤታማ ስራዎችን መስራት አንደሚገባ የጉራጌ ዞን ምክር ቤት አስታወቀ።

ምክር ቤቱ ከዞኑ ሴቶችና ህጻናት መምሪያ ጋር በመቀናጀት ሴቶች የመሪነትና የውሳኔ ሰጪነት ሚና አስመልክቶ ለኮከስ አባላት ሰልጠና በወልቂጤ ሰጥተዋል ።

የዞኑ ሴት ተመራጭ ህብረት አባላት የ2016 የ1ኛ ግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸምና የ2ኛ ግማሽ ዓመት እቅድ ላይ ዉይይትም ተካሄዷል ።

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ክብርት ወይዘሮ ልክነሽ ሰርገማ እንደተናገሩት ሴቶች በማህበራዊ፣ በፖለቲካዊና በኢኮኖሚ ያላቸውን ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የሴቶች ኮከስ ማጠናከር እና ውጤታማ ስራዎችን መስራት ይገባል ብለዋል።

የኮከሱ መጠናከር ዘርፈ ብዙዎች ጠቀሜታ እንዳለው የተናገሩት ክብርት አፈ ጉባኤዋ ሴቶች በህግ አውጪ ደረጃ ያላቸው ተሳትፎ የተሻለ ቢሆንም በህግ አስፈጻሚና ተርጓሚ ደረጃ ላይ ያላቸው ተሳትፎ ለማሻሻል ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ሴት አመራሮች በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ኮከሱ ጠንካራ አባላት ለማፍራትና የሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ በመሆኑ የራሱ የገቢ ምንጭ ማፍራት ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።

በዞኑ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ለመከላከል የኮከሰ አባላት ጉልህ ሚና መጫወት ያሉት ክብርት አፈ ጉባኤዋ ወ/ሮ ልክነሽ ሰርገማ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች የፈጸሙ ግለሰቦች በህግ እንዲጠየቁ እና መሰል ድርጊቶች ዳግም እንዳይፈጸምባቸው ለመከላከል አደረጃጀቶችን ከማጠናከር በተጨማሪ የፍትህ አካላት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት እንዲሰጡ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

የኮከሱ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሔሪያ ወርቁ የኮከሱ የ2016 የ1ኛ ግማሽ አመት አፈጻጸም ሪፖርት ሲያቀርቡ እንዳሉት ኮከሱ ከተቋቋመ ወዲህ የሴቶች ተሳትፎ እያደገ መምጣቱና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በሚፈለገው ደረጃ ባይሆንም በርካታ ስራዎችን መከናወናቸው ተናግረዋል ብለዋል።

እንደ ወ/ሮ ሔሪያ ወርቁ ገለፃ የኮከሱ የውስጥ ገቢ የማሳደግ፣ የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር የማጠናከር፣ የወረዳና የከተማ የኮከስ አደረጃጀር የመደገፍና የመከታተል ስራ እንዲሁም ሁለንተናዊ የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት በሚያሳድጉ ተግባራት ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ባቀረቡት እቅድ አመላክተዋል ።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ዉይይት መደረጉና ስልጠና መሰጠቱ ክፍተቶቻቸው በመሙላት በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት መነሳሳትን እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል።

አክለውም ተሳታፊዎቹ ሴቶች በማህበራዊ ዘርፍ በሚያደርጉት ንቁ ተሳትፎ በትምህርት፣ በእናቶችና ህጻናት ደህንነት፣ በግልና አካባቢ ንጽህናና በሌሎች ተግባራት የላቀ ውጤት ማስመዝገብ እንዳለባቸው አብራርተዋል።

በሌላ በኩል ሴቶች በኢኮኖሚው፣ በማህበራዊና በፓለቲካው ያላቸው ተሳትፎና ተጠቃሚነት በይበልጥ እንዲሻሻል በቀጣይ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል ማለታቸው የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *