የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሴቶች ልማት ቡድን የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ አስታወቀ።

ጥር 9/2015 ዓ.ም
የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሴቶች ልማት ቡድን የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ አስታወቀ።

በጉራጌ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ አስተባባሪነትና በክልሉ በተገኘ ድጋፍ ለግምባር ቀደም ልማት ቡድኖች የ45 ቀን ጫጩት ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።

የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ ምክትል ሀላፊ ወይዘሮ አርሺያ አህመድ በዚህ ወቅት እንደገለፁት ከአሁን በፊት የሴቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራት ሲከናወኑ እንደነበር አስረድተዋል።

ከክልሉ ሴቶችና ህፃናት ቢሮ በተገኘ ድጋፍ የ45 ቀን ዶሮዎች ከየወረዳው ለተመረጡ ልማት ቡድኖች ድጋፍ መደረጉን የገለፁት ወይዘሮ አርሺያ ዶሮዎቹን በተገቢው በመንከባከብ ለተሻለ ተግባር መነሳሳት እንዳለባቸው ወ/ሮ አርሺያ አሳስበዋል።

የሴቶችን ኢኮኖሚ ለማሳደግና የገቢ ምንጫቸው እንዲዳብር መሰል ድጋፎች ማጠናከርና መደገፍ እንደሚገባ ገልጸዋል።

አራጋው ደምሌ ከጉመር እና ጌትነት ዋለ ከቸሀ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጽህፈት ቤት የመጡ ሲሆን የተደረገው ድጋፍ መንግስት ለልማት ቡድኖች የሰጠውን ትኩረት ማሳያ መሆኑን አብራርተዋል።

የልማት ቡድኖችን መደገፍ የሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ሚናው የጎላ በመሆኑ ለወደፊቱ መሰል ድጋፎች ተጠናክሮ እንዲቀጥል በመጠየቅ አሁን ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸው አቅርበዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *