የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ በማልማት የህብረተሰቡን ኑሮ ለማሻሻና ፈጣን እድገት ለማስመዝገብ የሴክተሩና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለባቸው የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ

የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ በ2013 አመተ ምህረት የስራ አፈጻጸምና የ2014 አመተ ምህረት እቅድ ዝግጅት ዙሪያ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ አመታዊ የምክክር ጉባኤውን በወልቂጤ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የጉራጌ ዞን አስተዳደር ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሰፋ አካሉ እንዳሉት አገራችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ብዙ ያልተሰራበት ከመሆኑ አንፃር በቀጣይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ዘርፉ የሚያበረክተው አስተዋፅዖ እንዲጎለብት መደረግ አለበት ብለዋል፡፡

ያለንበትን ተጨባጭ ሁኔታ ለመረዳት ሳይንስና ቴከኖሎጂ ወሳኝ ነው የሚሉት አቶ አሰፋ ጥራትና ፍጥነትን በማጣመር አለም በአሁኑ ሰዓት ሳይንስና ቴክኖሎጂን በመጠቀም አስገራሚ ለውጥ እያስመዘገበች ትገኛለች ብለዋል፡፡

ተቋሙ ለብዙ ችግሮቻን መፍትሔ መስጠት የሚችል በመሆኑ ሁሉም የዘርፉ ባለሙያና ባለድርሻ አካላት ሙያዊ ግዴታቸውን በተገቢው እና በቅንነት መወጣት እንዳለበት አቶ አሰፋ ገልፀዋል፡፡

የጉራጌ ዞን ሳይንስና ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ እንደገለፁት አሁን ላይ በቴክኖሎጂው ዘርፍ እንደሀገር ጥሩ እመርታ እየታየበት ቢሆን እንደዞናችን መምሪያው የተጣለበት ኃላፊነትና ተግባር ከባለድርሻ አካለት ጋር በመሆን በቅንጅት መስራት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

አቶ ደምስ አክለው በቀጣይ ከሪፖርት ጥራት ጀምሮ ለተግባራቶችን ሁሉ ትኩረት በመስጠጥ ቴክኖሎጂዎችን ለተቋማትና ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ሁለተናዊ እድገት ማፋጠን አለብን ብለዋል፡፡

በምክክሩ መድረክ የተሳተፉ አካላተረ በሰጡት አስያየት በቴክኖሎጂ ዘመን የድሮውን ይዘን መጓዝ የለብንም በማለት የዘመነ የቴክኖሎጂ ሽግግር በሁሉም መዋቅር ተደራሽ መሆን አለበት ብለዋል፡፡

ሴክተሩ የማስፈፀም አቅም ለማሳደግና በዘርፉ ህብረተሰቡን ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል ያለበት የሰው ኃይል፣ የበጀት፣ የቁሳቁስ ችግር ለመፍታት ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው መሰራት አለባቸው ብለዋል፡፡

በመጨረሻም መምሪያው የ2014 እቅድ ዙሪያ ከወረዳዎችና ከከተማ አስተዳደር መዋቅሮች ጋር ሰፊ ውይይት በማድግ ተፈራርመዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *