የሰላም መንገድ እንዳይዘጋ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ህውሃትን ወደሰላም መንገድ ሊያመጣው እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት አስታወቀ ።

ጷግሜ 1/2014

የሰላም መንገድ እንዳይዘጋ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ህውሃትን ወደሰላም መንገድ ሊያመጣው እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት አስታወቀ ።

ለሶስተኛ ጊዜ የህውሃት ቡድን የከፈተብንን ጦርነት በማውገዝ ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ደጀን መሆናቸውን የወልቂጤ ከተማ እና የአበሽጌ ወረዳ ሴቶች ገለፁ ።

የጉራጌ ዞን ሴቶች ሊግ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ ዝናሽ ሀይሌ እንደገለፁት የህውሃት ቡድን ህዝቡ ላይ እያደረሰ ያለውን የጥፋት እንቅስቃሴ በማውገዝ እና ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ደጀን ለመሆን ሴቶች ግምባር ቀደም መሆን ይገባል ።

ከአሁን በፊት በዞኑ ያሉ ሴቶች ሰምባች ምግብ በማዘጋጀት ለሰራዊቱ አጋርነታቸውን አሳይተው እንደነበር በመጥቀስ አሁንም ለሶስተኛ ጊዜ በፈፀመብን ጥቃት ሳቢያ ሊከሰት የሚችለውን ሀገራዊ ቀውስ ከግምት ውስጥ በማስገባት ከወዲሁ በአንድነት መቆም እንደሚገባ አመላክተዋል ።

በዚህም ዝግጅት ከ2 ሺህ 4 መቶ ኩንታል በላይ በሶ፣ ከ5 መቶ በላይ ሰንጋዎችንና ከ1 ሺህ 3 መቶ በላይ ፍየል እና በግ ለማሰባሰብ አቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን ጠቁመዋል ።

የወልቂጤ ከተማ ሴቶች እና ህፃናት ፅህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ ፈቲሀ ሱልጣን በበኩላቸው ከአሁን በፊት ለሁለተኛ ጊዜ በተከፈተብን ጦርነት ላይ የተደረገውን ድጋፍ በማስታወስ ወረራውን አቁሞ ወደ ሰላም ድርድሩ እስኪመለስ ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል ።

የጦርነቱ የመጀመሪያው ገፈት ቀማሽ ሴቶች እና ህፃናት መሆናቸውን በመግለፅ ድርጊቱን በማውገዝ ከመከላከያ ጎን በመቆም አጋርነታቸውን ማሳየት እንዳለባቸው አሳስበዋል ።

አሽረቃ ሁሴን ፣ ፋጤ ሂርጰሳና ቅባትነሽ ገብረ መስቀል በጋራ በሰጡት አስተያየት ያለን ሀገር አንድ በመሆኗ ለሀገራችን ሰላም መከበር የምንችለውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነን በማለት ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም በነበረው ወረራ ኢትዮጽያውያን በጋራ የቆምንበት ወቅት እንደነበር በማስታወስ በቂ እድሜና ወታደራዊ ስልጠና የሌላቸው ህፃናትን ወደ ጦርነት መማገዱን ሊያቆም እንደሚገባ ገልፀዋል።

ለመከላከያ ሰራዊቱም በስንቅ ዝግጅትም በአካልም በመገኘት ድጋፋቸውን እንደሚያደርጉ ገልፀዋል ።

ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Twitter:- https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *