የማዕከላዊ የኢትዮጵያ የመንገዶች ባለስልጣን እና የጉብሬ የገጠር መንገድ ዲስትሪክት ጋር በመሆን በወልቂጤ ማረሚያ ቤት ስር ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች የምገባ፣ የአልባሳትና የቁሳቁስ ድጋፍ በዛሬው ዕለት አደረገ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ምክትልና የሪጎላተሪ ዘርፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ወሰን ባሻ በወልቂጤ ማረሚያ ተቋም በተገኙበት ወቅት እንደተናገሩት የበጎ ፍቃድ ተግባራ የአንድ ወቅት ስራዎች ብቻ ሳይሆኑ አመቱን ሙሉ በመተግበር የሌሎች ድጋፍ የሚሹ ወገኖች በመርዳት ማህበራዊ ኃላፊነታችን ልንወጣ ይገባል፡፡

እንደ ሀገር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚኖሩ ወገኖች አለኝታነትን ለመግለጽ የተጀመረው የምገባ መርሀግብር ለማስቀጠል የክልሉ መንገዶች ባለስልጣን በወልቂጤ ማረሚያ ተቋም ስር ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች የምሳ ምገባ፣ የአልባሳትና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ መቻላቸው አቶ ወሰን ገልጸዋል፡፡
በቀጣይም ተቋሙ ያለበት ክፍተቶችን በመለየት የበኩላቸውን እገዛ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የጉብሬ ዲስትሪክት ስራ አስኪያጅ አቶ አሰፋ አካሉ እንደገለጹት በማረሚያ ቤት ውስጥ ደጋፊና ጧሪ የሌላቸው ወገኖችን መርዳት እጅግ አስፈላጊና ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል።

በክረምት ወራት የበጎ አድራጎት ስራ ባሕል እየሆነ መምጣቱን ተከትሎ የክልሉ መንገዶች ባለስልጣንና የጉብሬ ገጠር መንገድ ዲስትሪክት የስራ ሀላፊዎች እና ሰራተኞች ስው ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው በሚል ተነሳሽነት ማረሚያ የሚገኙ ወገኖችን ለመጠየቅና በተቻለ አቅም ለመደገፍ መነሳታቸውን ተናግረዋል።

አክለው ም በድንገተኛ ስህተት ማረሚያ የሚገቡ ወገኖች የእርምት ጊዜያቸውን ጨርሰው ሲወጡ መልካም ስነ-ምግባር እንዲኖራቸው ለማስቻል እና አሁን ላይ ወገን እንዳላቸው ለማሳየት ነው ብለዋል ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ ማረሚያ ተቋም ኃላፊ ኢንስፔክተር ሚስባ ግራኝ እንደገለጹት ታራሚዎች ከስህተታቸው ታረመውና ጥሩ ስነ ምግባር ይዘው ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ተቋሙ ሰፊ ስራ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

ታራሚዎች በቆይታቸው ጊዜ በቂ እውቀት እና ክህሎት እንዲኖራቸው ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመቀናጀት የክህሎት ስልጠናዎችን በመስጠት እንዲሁም በማህበር በማደራጀት ስራ እንዲሰሩ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል ኢንስፔክተር ሚስባ ።

የክልሉ መንገዶች ባለስልጣንና የጉብሬ የገጠር መንገድ ዲስክሪት የስራ ሀላፊዎችና ሠራተኞች ላደረጉት ድጋፍና ምግብ አመስግነው ተቋሙ በርካታ ታራሚዎችን እያስተናገደ በመሆኑ በሚበጀትላቸው በጀት ብቻ ወጪያቸውን መሸፈን እያዳገደ በመሆኑ እና ክፍተቶች በመኖራቸው ሌሎችም ተቋማትና ግለሰቦች መሰል ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ ይጠይቀዋል።

ታራሚዎችም በሰጡት አስተያየት የተቋሙ የስራ ሃላፊዎችና አጠቃላይ ሰራተኞች የአልባሳት፤የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እንዲሁም የምሳ ፕሮግራም በማዘጋጀታቸው መደሰታቸውን ተናግረው ሌሎችም ተቋማትና ግለሰቦች ጥያቂ ለሌላቸው ወገኖች ድጋፍና እንክብካቤ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል ።

በመጨረሻም እየተቋሙ የስራ ሀላፊዎችንና ሰራተኞች ታራሚውን ከመመገብና ከማልበስ እንዲሁም የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ከመለገስ ባለፈ የወልቂጤ ማረሚያ ተቋም ተዛዙረው ጎብኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *