የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ በእውቀት፥ በክህሎትና በአመለካከት የበለፀገ ዜጋ ለማፍራት እያደረገ ያለው ተግባር አበረታች መሆኑ የክልሉ ምክር ቤት ገለጸ።


አካዳሚዉ በመንግሥት ተቋማት ግንባር ቀደም ፈፃሚዎች ለማብቃት በወልቂጤ ከተማ ሲሰጥ የነበረዉ ስልጠና ተጠናቋል።

የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ግዛቸዉ ዋሌራ እንደተናገሩት አመራር አካዳሚው ዘመኑን የሚመጥን ስብዕናን ለመላበስ ወጣቱ በዕዉቀት፣ በአመለካከትና በተግባር ብቁና ተወዳዳሪ ለማድረግ እየሰራ ያለው ተግባር የሚበረታታ መሆኑን ገልጸዋል።

ለሁለተኛ ጊዜ እየተሰጠ ያለው ስልጠና መነሳሳትን የፈጠረ እደሆነና ወጣቱ ምክንያታዊነትን፣ ሚዛናዊነትንና የግል ህይወቱን በመርህ መምራት ያስችላል ብለዋል።

አክለውም ወጣቱ የስሜት ስክነትና ራስን የመግዛት ክህሎቱን እንዲያጎለብት በጋራ መስራት እና የተደራጀና የተቀናጀ አሰራር እንደሚያስፈልግ በማመን መንቀሳቀስ እንዳለበትም ተናግረዋል።

የአገልጋይነት መንፈስ በማዳበር ተግዳሮትን ተጋፍጦ ለማሸነፍ እና በፈተና ለመጽናት ራስን ለአዎንታዊ ነገሮች ማዘጋጀት እንዳለበት ገልጸዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ብላቱ በበኩላቸው የሀገር ግንባታ የዜጎች የጋራ ፕሮጀክት በመሆኑ ሰልጣኞቹ በክልሉ ብሎም በሀገሪቱ ዕድገት አሻራቸውን እንዲያኖሩ ታስቦ ከሁሉም የክልሉ አካባቢዎች የተውጣጡ ሰልጣኞች መሳተፋቸውን አስረድተዋል ።

ሁሉም በየተሰማራበት መስክ እህታማችነትና ወንደማችነትን በማዳበር አርአያነት ያለው መሪ መሆን እዳለበት አስረድተዋል።

የአለም ፖለቲካ በመረዳት ባህልን ለማሻሻል ከሰልጣኞች ብዙ እንደሚጠበቅም አቶ ተስፋዬ አመላክተዋል።

የአካዳሚዉ ምክትል ዳይሬክተር እና የስልጠና ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱልበር ኡስማን በስልጠናው የተገነባዉ አቅም ሥራ ላይ መዋሉንና ፋይዳዉን በቀጣይ አካዳሚዉ ክትትል ያደርጋል ብለዋል።

ሰልጣኞች ወደመጡበት ተቋማትና መዋቅሮች ሲመለሱ አርአያ በመሆን ተከታይ እንዲያፈሩም ዳይሬክተሩ መልእክት አስተላልፈዋል።

ከአሰልጣኞች መካከል በላይነህ ሰልማንና ሙኒራ ሞሳ ከጉራጌ፥ መስታወት አማዶ ከከምባታ
አብደላ ሀጅርታ ከሀላባ ዞን ይገኙበታል። ስልጠናው የህይወት ክህሎትና የመፈጸም አቅምን ለማጎልበት ወሳኝ ነዉ ብለዋል።

ስልጠናዉ በሀገር ግንባታ ሂደት ጉልህ ሚና ባላቸዉ ወጣቶችና ሴቶች ላይ ማተኮሩ ዉጤታማነቱን ያጎላዋልም ነው ያሉት።

በየአካባቢያቸው ሌሎች ልምዳቸውን እደሚያጋሩም ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *