የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማና በቀቤና ልዩ ወረዳ አሁናዊ የፀጥታ ሁኔታ ገምግም የቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጧል።

መድረኩ በክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ በክቡር አቶ ተመስገን ካሳ እና በፍትህ ቢሮ ኃላፊ በክቡር አቶ አክመል አመዲን በጋራ መርተውታል።

በመድረኩ ኮሚ/ር ሺመልስ ካሳ የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነርና የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች አቶ ላጫ ጋሩማ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ አቶ ሞሳ ኢዶሳ የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና

የጊዜያዊ ኮፖስት አመራሮችና አባላት በተገኙበት የኮፖስቱ የእስካሁን አፈጻጸም ራፖርት በኮ/ሚ ቦጋለ ቀርቦ ተሳታፊዎች ሰፊ ወይይት በማድረግ ጥንካሬዎችና ጉድለቶች የተለዩ ሲሆን ኮ/ፖስቱ ቀደም ሲል የተፈጠረው ብጥብጥ በማስቆምና የተረጋጋ አካባቢ ለመፍጠር የሚያስችል ባለ 6 ግብ እቅድ እና ዝርዝር ተግባራት ለይቶ በማቀድ ወደ ተግባር መግባቱን በሪፖርቱ የተጠቀሰ ሲሆን እነዚህ ግቦችን ለማሳካት በተሰሩ ስራዎች ነዋሪው በሰላም ገብቶ እንዲወጣ እና አንፃራዊ ሰላም እንዲፈጠር መደረጉን ተብራርቷል።

ሆኖም በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት እንዳይፈጠር የሚሰሩና ብጥብጥን ለዘረፋ መጠቀሚያ ለማድረግ በተደራጀ መልኩ የሚንቀሳቀሱ የግጭት ነጋዴዎች ቀን ከሌት አሳቻ ወቅቶችን ጠብቀው ትንኮሳ በመፍጠር፣ በመዝረፍ ተራ የውምብድና ስራ በመስራት ለነዋሪውና ለጸጥታ ሀይሉ ፈተና ሆኖ መቆየቱን እና ይህንን የወንጀል ድርጊት በተቀናጀ እና በማያዳግም መልኩ ለማስቆም እርምጃ መወሰድ እንዳለበት አስንኦት ተሰጥቶታል።

የተዘረፈን ንብረት ከማስመለስ አንጻር ጥሩ ጅምሮች መኖራቸውና ቀሪ ስራዎችም በተለይም ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገልጿል።

ከዚህ በመነሳት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ተመስገን በሰጡት የቀጣይ አቅጣጫ የወልቂጤና አካባቢዋ ሰላም ለማረጋገጥና ብሎም ሕዝባችን ከደህንነት ስጋት ለማውጣት
የጸጥታ አመራሩ የአስተሳሰብና የአመለካከት አንድነት ወሳኝ በመሆኑ ለውጥ ማምጣት ይጠበቅበታል።

ሌላው ሕዝባዊነትና ገለልተኝነት እንዲሁም ስራን ተቀናጅቶ መስራት እንደሚያስፈልግ
በዘራፊዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ ትንኮሳ ዜሮ ማድረግ፣ ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን ለህግ ማቅረብ ተፈናቃዮችን መመለስ፣ የዜጎች በነፃነት የመንቀሳቀስ መብትን ማረጋገጥ የቀጣይ የፀጥታ መዋቅሩና የአመራሩ ተግባር በመሆኑ በጥብቅ ድስፕሊን እንዲመራ መመሪያ ሰጥቷል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *