የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለመምህራን እየተሰጠ በነበረው ስልጠና ማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው ስልጠናውን ጎብኝተዋል።


በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በአዲሱ ስርአተ ትምህርት 12ኛ ክፍል ለሚያስተምሩ መምህራን እና አመራር ለ3 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ።

ርእሰ መስተዳድሩ በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ እየተከናወኑ ያሉ የማህበረሰብ አቀፍ ስራዎችን የተመለከቱ ሲሆን ከዩኒቨርስቲው የአመራር አካላት ጋርም ውይይት አድርገዋል።

ዩኒቨርስቲው ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እያበረከተ ላለው አስተዋጽኦ ያደነቁት ርእሰ መስተዳድሩ መምህራን፣ ርእሳነ መምህራንና የትምህርት አመራሩ በአዲሱ ስርአተ ትምህርት በቂ ግንዛቤ በመጨበጥ የታሰበው ውጤት እንዲመጣ መትጋት ይጠበቅባችኋል ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትልና የትምህርት ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አስከብር ወልዴ እንደተናገሩት ስልጠናው የተማሪዎች ስነ ምግባር እና ውጤት ማሻሻል ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን በዚህ ስልጠና የአዲሱ ስርአተ ትምህርት ትውውቅ፣የፈተና ቢጋር አወጣጥና ኢንስትራክሽን ሊደር ሺፕ በሚሉ እርሰ ጉዳዮች በሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ስልጠናው እንደሚሰጥ ተናግሯል።

ከጉራጌ ፣ከምስራቅ ጉራጌ ፣ከየም ዞኖች እና ከቀቤና ልዩ ወረዳ ለተውጣጡ 988 ሰልጣኞች12ኛ ክፍል ለሚያስተምሩ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የመማሪያና ማስተማሪያ መጽሀፍት ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና እንደነበር አቶ አስከብር ወልዴ ገልጸዋል።

በክልሉ በወልቂጤ፣በዋቸሞ እና በወራቤ ዩንቨርሲቲዎች በሚሰጠው ስልጠና 2ሺ841 መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮ መሳተፋቸውም አቶ አስከብር አመላክቷል።

የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቴ ወ/ማረያም በበኩላቸው ክልሉና የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ለትምህርት ውጤት መሻሻል የሚያደርጉት ተሳትፎ የሚበረታታ ነው ብለዋል።

አክለውም ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ወደ ታች ወርዶ ተግባራዊ እንዲሆን ይሰራል ያሉት አቶ መብራቴ ስልጠናው በየደረጃው የ2ኛ ደረጃ መምህራን ከስርአተ ትምህርቱ ባለመተዋወቃቸው በመማር ማስተማሩ ሂደት ያለው ተፅኖ አስመልክተው ሲያነሱት የነበረው ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ ነው።

በ2016 12ኛ ክፍል የሚያስፈትኑ ትምህርትቤቶች ርእሰ መምህራን እና ሱፕርቫይዘሮች የተሳተፉበት ሲሆን
እንደ ጉራጌ ዞን ደግሞ 6መቶ 44 ሰልጣኞች ስልጠናው ሲከታተሉ እንደነበር አመላክተዋል።

በስልጠና ወቅት አግኝተን ያነጋገርናቸው ሰልጣኞች እንዳሉት ስልጠናው ከዚህ በፊት የነበረው የትምህርት ጥራት ችግር የሚቀርፍና የትምህርት ውጤት ስብራት ሊጠግን የሚችል እንደሆነ ገልጸዋል።

የተዘጋጀ አዲሱ የስራአተ ትምህርት መጸሀፍና ስልጠና ተማሪዎች በቴክኖሎጂ የተደገፈና በሳይንስ ትምህርቶች ላይ አትኩረው እንዲሰሩ የሚረዳ መሆኑና ቀጣይ በአገኙት እውቀት እስከ ታች ወርደው ተግባራዊ እንደሚያደርጉ አስታወቀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *