የማምረቻና መሸጫ ቦታዎች በፍትሀዊነት በማከፋፈል ስራ አጥ ዜጎችን በግብርናው፣ በኢንዱስትሪዉ እና በአገልግሎት ዘርፍ ስራ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ ።

የጉራጌ ዞን ስራ እድል ፈጠ

የደቡብ ክልል የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢረዳ ብርሀኑ በመክፈቻው ስነ-ስርአት ወቅት እንዳሉት ስራ አጥ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን በግብርናው፣ በኢንዱስትሪዉ እና በአገልግሎት ዘርፍ እንዲሰማሩ እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል ።

ባዛርና ኤግዚቢሽን ለአምራች ኢንተርፕራይዞች ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅና ለመሸጥ እንዲሁም የገበያ ትስስር ለመፍጠር ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል ።

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የስራ እድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን በወቅቱ እንደገለጹት የማምረቻና መሸጫ ቦታዎች የማይመለከታቸው የማህበረሰብ ክፍሎች እየተጠቀሙበት በመሆኑ እያስመለሱ እንደሆነና በቀጣይም በፍትሀዊነት የማከፋፈል ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ስራ አጡን በማህበራት በማደራጀትና አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ወደ ስራ ለማሰማራት በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

በመድረኩ ካነጋገርናቸው መካከል ቀመሪያ ሀሰን ከቡታጅራ ከተማ እና ሀሰን ሳኒ ከወልቂጤ ከተማ በእንጨትና ብርታብረትስራ እና በጨረቃጨርቅ ስራ የተሰማሩ ሞዴል ማህበራት ናቸው ።

ከትንሽ ነገር ተነስተዉ ከመንግሥት በተደረገላቸው ማምረቻና መሸጫ ቦታ፣ ሞያዊ ድጋፍ እና ሌሎችም አስፈላጊ ነገሮች በማገኘታቸው ዛሬ ላይ የተሻለ ደረጃ ላይ መድርሳቸውን ተናግረዋል ።

ኤግዚቢሽን እና ባዛር በመዘጋጀቱ ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅ እና ለመሸጥ እንደሚረዳቸው አስተያየት ሲጪዎች ገልጸዋል ።

የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ሞዴል ለሆኑና ለተሸጋገሩ ኢንተርፕራይዞች፣ተቋማት፣ ኮሌጆች ፣የእውቅና፣ የዋንጫና ሌሎችም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ።

በመክፈቻ መድረኩም የክልል፣ የዞን፣የወረዳና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች፣ ሞዴል ኢንተርፕራይዞችና የደረጃ ሽግግር የሚያደርጉ ማህበረትና ባለ ድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *