የማህጸን ወደ ውጭ የመውጣት ችግር አስቀድሞ ለመከላከል ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስታወቀ።

ሆስፒታሉ ዊሊንግ ኦፍ ሂሊንግ ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር በመሆን ለማህጸን ውልቃት ችግር ተጋላጭ ለሆኑ ለአንድ መቶ እናቶች ነጻ የህክምና አገልግሎት መስጠቱን ተመልክቷል።

የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሸምሱ አማን በበኩላቸው ህመሙ ታክሞ መዳንና አስቀድሞ መከላከል የሚቻል ሲሆን በእርግዝና ወቅት የቅድመ ወሊድ ክትትል፣ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት፣ የስራ ጫና መቀነስ ይጠበቅባቸዋል።

እንደ ኃላፊው ገለጻ ዞኑ የማህጸን ውልቃት ችግር ከሚስተዋልባቸው አካባቢዎች አንዱ በመሆኑ በችግሩ የሚሰቃዩ እናቶች አስፈላጊ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ የዞኑ አስተዳደር ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

በመሆኑም በየ አመቱ የዞኑ አስተዳደር ለማህጸን ውልቃት ህመም ተጋላጭ የሆኑ እናቶች የህክምና አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ በጀት እየመደበ የህክምና አገልግሎት ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

በቀጣይ የእናቶች ጤና ለመጠበቅ ከአጣጥና ከቡታጅራ ሆስፒታሎች ጋር በመቀናጀት እንደሚሰራ ኃላፊው አክለው ገልጸዋል።
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልና የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስክዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር አብድራሂም በድሩ ሆስፒታሉ ከመማር ማስተማር ስራው በተጨማሪ የህብረተሰቡ ጤና ለማጎልበት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።

ሆስፒታሉ በህክምናው ዘርፍ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች አንዱ የማህጸን ውልቃት ህክምና ሲሆን ከረጂ ድርጅቶች ጋር በመሆን ለማህጸን ውልቃት ችግር ተጋላጭ ለሆኑ ለአንድ መቶ እናቶች ነጻ የህክምና አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለ አብራርተዋል።

የማህፀን ወደ ውጭ መውጣት ችግር በብዙ ሴቶች የሚከሰት ቢሆንም ተጋላጭ የሆኑ ሴቶችን አስቀድመው የህክምና ክትትል በማድረገ በቀላል ህክምና እንዲድኑ ያስችላቸዋል ብለዋል።

የማህፀን ወደ ውጭ መውጣት ችግር እንዲከሰት በምክንያትነት የሚጠቀሱት እርግዝናና ወሊድን፣ ሸክም ማብዛት፣ የአመጋገብ ስርዓት አለመዳበርና ሌሎች ምክንያቶች እንዳሉ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ረቢ አሊ ኡመር የማህጸንና ጽንስ ስፔሻሊስት ሲሆኑ የማህፀን መውጣት ችግር ማለት የውስጠኛው የማህፀን ክፍል ቦታውን በመልቀቅ ወደ ውጭ መውጣት ማለት ሲሆን ይህ ችግር በአብዛኛው የውስጠኛውን የማህፀን ክፍል በቦታው የሚይዙት ጡንቻዎች በተለያዩ ምክንያቶች መደበኛ ስራቸውን መስራት ሳይችሉ ሲቀር የሚከሰት የህመም አይነት ነው ብለዋል፡፡

የማህጸን ወደ ውጭ መውጣት ችግር ኖሮባቸው ህመማቸውን ደብቀው የሚኖሩ በርካታ እናቶች ቤት ውስጥ የሚገኙ በመሆኑ ግንዛቤ ተፈጥሮላቸው የህክምና አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ መሰራት አለበት ብለዋል።

በዊሊንግ ኦፍ ሂሊንግ የፕሮግራም አስተባባሪ ዶክተር አዊና በቀለ ፕሮጀክቱ ህብረተሰብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።

የማህጸን መውጣት ችግር በከፍተኛ ሁኔታ ተስፋፍቶ የሚገኝ ሲሆን በሴቶች ላይ ማህበራዊ፣ ኢኪኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጫና ያሳድርባቸዋል ብለዋል።

ፕሮጀክቱ በዚህ ህመም የሚሰቃዩ እናቶች ከህመማቸው ለማሳረፍ ከዞኑ ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆናቸው ተናግረዋል።
ከህክምናው በተጨማሪ ለአራት ጋይናኮሎጂዎች የስራ ላይ ስልጠና ከመስጠት ጎን ለጎን የእውቀት ሽግግርና ለህክምና አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶች ድጋፍ እንደሚያደርግ አስረድተዋል።

ኦንሲ ሉካ የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ ሲሆኑ በማህጸን ውልቃት ችግር ውስጥ የሚገኙ ሴቶች ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭ እንደሚሆኑ አብራርተዋል።
የህክምና አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ እናቶች እንደተናገሩት የተከሰተባቸው የማህጸን ውልቃት ችግር በእለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ፈጥሮባቸው እንደነበር ቸብራርተዋል።

ችግሩ ከተከሰተባቸው መቆየቱን ተከትሎ በጤናቸው ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደሩን የተናገሩት ተጠቃሚዎቹ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ወደ ጤና ተቋም አለመሄዳቸውና የህመማቸው መረጃ በድብቅ ማቆየታቸው ይበልጥ እንደጎዳቸው አብራርተዋል።

ሆስፒታሉ ያደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸው አቅርበው የዚህ ህመም ተጋላጭ የሆኑ ሴቶች የህክምና አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን አለባቸው ብለዋል ሲል የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

  • አካባቢህን ጠብቅ!
  • ወደ ግንባር ዝመት!
  • መከላከያን ደግፍ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *