የማህበረሰብ አቅፍ ስፖርት በሀገራዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ሚናው የጎላ በመሆኑ ባህል አድርጎ መስራት እንደሚያስፈልግ የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ።

የጎዳና ስፖርት ፍቅርን ወዳጅነትና አንድነትን ከማጠናከሩ በላይ ጤናማና ምርታማ የማህበረሰብ ክፍል ይፈጥራል በሚል የማስ ስፓርት በዛሬው እለት በወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አወል ጁማቶ ስፖርት ለማህበራዊ፣ለኢኮኖሚ፣ለፖለቲካ ለአንድነት፣ለሰላምና ለፍቅር ብሎም ለተለያዩ ክንዋኔዎች ሚናው የጎላ በመሆኑ ባህል አድርጎ መስራት እንደሚያስፈልግ አሳስብዋል።
አክለውም ስፖርት ለጤንነት የማይተካ ሚና ያለው በመሆኑ ይህንን ታሳቢ በማድረግ የማስ ስፖርትን ለሁሉም ማህበረሰብ ለማስተማር አደባባይ ለወጡ ስፖርተኞች ምስጋና አቅርበዋል።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትልና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አደም ሽኩር በበኩላቸው የማህበረሰብ አቀፍ ስፖርት አስፈላጊ በመሆኑ ከፌደራል እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራበት ይገኛል።

ዜጎች ጤናቸው የተጠበቀ እንዲሆንና ምርታማ የህብረተሰብ ክፍሎች ለማፍራትና ስፖርቱ ባህሉ ያደረገ ህብረተሰብ ለመፍጠር አላማ ያለው ነው ብለዋል።

በወረዳና ከተሞች የማስ ስፖርቱን የጀመሩት አጠናክረው እንዲቀጥሉና ያልጀመሩት ደግሞ እንዲጀምሩ ይደረጋል ብለዋል አቶ አደም ሽኩር

በዞናችን በ21ዱ መዋቅሮች እስከ ሰኔ 10 ድረስ የሚቆይና 1መቶ 68ሺ ህዝብ ያሳተፈ የማስ ስፖርት ፕሮግራም እንዲካሄድ ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግሯል።

አቶ አደም አክለውም ጤናማ ህብረተሰብ ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ሁሉም ህብረተሰብ ግንዛቤ ኖሮት እንዲሰራ በሚዲያና የቅስቀሳ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ አመላክተዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ምክትል የመንግስት ተጠሪ አቶ ቃልአብ ደመቀ በንግግራቸው ወቅት እንደገለፁት ስፖርት በአንድ ሀገር እድገት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ሚና የሚጫወት በመሆኑ ዘርፉን ለማሳደግ መንግስት በቁርጠኝነት እየሰራበት እንደሚገኝ ጠቁመው እንዲህ አይነት የማነቃቂያ ስፖርቶች ሲከናወኑ ዘርፉ ይበልጥ እንዲጎላ ያደርገዋል ብለዋል።

የተጀመረው የጎዳና ስፖርት በየቤታችን፣በአካባቢያችንና በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ አቶ ቃል አብ መክረዋል።

የቡሩሲኒ ማርሻል አርት መስራች ማስተር ጥላሁን ግርማ፣ የቀርጫት ኳስ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ዘመዴ በቀለ፣አቶ ፋንቱ ታደሰና ወጣት ማህሌት እንዳይላሉ የማስ ስፖርቱ ተሳተፊዎች ናቸው።
መሰል አይነት ስፖርቶች ሲሰሩ ጤናችን ከተለያዩ በሽታዎች ከመከላከል በተጨማሪ ሱስ ላለበት ሰው ከሱስ እንዲላቀቅ ጭምር ጉልህ ሚና ይጫወታል ሲሉ ገልጸዋል።

የማስ ስፖርት ለማጠናከር ማህበር ጭምር መመስረታቸው ገልጸው የማስ ስፖርት ከጀመሩ በኃላ የአካል ብቃታቸው እየጎለበተና ከአላስፈላጊ ውፍረት እንዲላቀቁ እገዛ አድርጎልናል ብለዋል።

በማህበራቸው አቅም ለሌላቸው ትጥቅ በመግዛትና ሌሎችም በጎ አድራጎት እንደሚያከናውኑ ተናግረው ስፖርቱ ቀጣይነት እንዲኖረው ገልጸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው ።
=ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *