የማህበረሰቡ ችግር የሚቀርፉ የሳይንስና የቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎችን በማበረታታትና በተገቢዉ በማልማት ዉጤታማ ስራ መሰራት እንዳለበት ተገለጸ።

የጉራጌ ዞን የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የሚሞክሩትን ስናበረታታ የሚችሉትን ይፈጠራሉ በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀዉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ዉድድርና ማበረታቻ /ኤግዚቢሽን/ስነ-ስርአት መድረክ በወልቂጤ ከተማ ተካሄዷል።

በመድረኩም የተገኙ የዞን የወረዳና የከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላቶች በተማሪዎች ፣በመምህራን ፣በኢንተርፕራይዞች፣ በኮሌጆችና በግል የተሰሩ የማህበረሰቡ ችግር የሚቀርፉ የፈጠራ ስራዎች ጎብኝተዋል።

በመድረኩ የተገኙት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንዳሉት ለዉድድር የቀረቡ የሳይንስና የቴክኖሎጂ የፈጠራ ዉጤቶች በጣም ጥሩ ጥሩና የማህበረሰቡ ችግር የሚቀርፉ እንደሆኑም ተናግረዋል።

አብዛኛ የፈጠራ ስራዎች የአርሶ አደሩ ችግር የሚቀርፉ የቴክኖሎጂ ዉጤቶች ሲሆኑ ከእርሻ ጋር ፣ ከሀርቨስቲንግ ጋር ያለዉ ችግር ከእንሰት ፕሮሰስ ጋር ያለዉን ችግር ለመቅረፍ የተፈጠሩ የቴክኖሎጂ ዉጤቶች በቀላሉ የአርሶ ደሩን ጉልበትና ጊዜ መቀነስ የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች እንደሆኑም ተናግረዋል።

ኢኖቬተር ኢዘዲን ካሚል ዛሬ ላይ ከሀገር አቀፍ እስከ አለም አቀፍ እዉቅና አግኝቶ በርካታ የፈጠራ ስራ ቴክኖሎጂዎች እንዳሉትም ተናግረዉ እነዚህም በዉድድሩ የማህበረሰቡ ችግር የሚቀርፉ ቴክኖሎጂ ይዘዉ የቀረበትን ማበረታታትና በተገቢዉ መደገፍ እንደሚገባም አብራርተዋል።

የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ እንዳሉት የማህበረሰቡ ችግር የሚቀርፉ የፈጠራ ስራዎችን በማበረታታትና በተገቢዉ በማልማት ለተጠቃሚዉ ተደራሽ እንዲሆኑ በትኩረት መሰራት እንዳለበት ተናግረዋል።

ዘመናዊ የመረጃ ቴክኖሎጂዎች በመዘርጋትና በማስፋት ህብረተሰቡ የግብርና ፣ የጤና ፣ የገበያ ፣የቱሪዝም ፣የባህል ፣የትምህርት እና የንግድ መረጃዎችን ኗአቅራቢያዉ እንዲያገኝ በማድረግ በገጠርና በከተማ ህብረተሰብ መካከል ያለዉን የዘመናዊ መረጃ ቴክኖሎጂ ክፍተት ማጥበብ ይገባል ብለዋል።

በሀገራችን ፈጣን ልማትና ዕድገት እንዲመጣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች ዘርፍ ማሳደግና በኢኮኖሚያዊ ፣በፖለቲካዊና በማህበራዊ እንቅስቃሴዉ ዉስጥ ያለዉን አስተዋጽኦ ማጎልበት እንደሚገባም አመላክተዋል።

የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዉድድርና ኤግዚቢሽን በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ያለዉን የተማሪዎች የመማር ፍላጎት ከማሳደጉም በተጨማሪ የተቀዛቀዘዉን የፈጠራና የፈጠራ ስራ እና የዉድድር ስሜትን ያነቃቃል ብለዉ በርካታ የፈጠራ ሀሳቦችና ችግር ፈቺ የፈጠራ ዉጤቶች በስፋት ይገኙበታል ብለዋል።

የደቡብ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምክትል የቢሮ ሀላፊ አቶ ሙሁዲን ሁሴን እንዳሉት ጉራጌ ዞን ጥሩና እምቅ የቴክኖሎጂ የፈጠራ ዉጤቶች በስፋት የሚገኝበትና በርካታ ኢኖቬተሮች መገኛም እንደሆነም ተናግረዉ በዉድድሩ ያዩት የፈጠራ ዉጤቶችና የማህበረሰቡ ችግር የሚቀርፉ ቴክኖሎጂዎች በስፋት የተመለከቱበት እንደሆነም ተናግረዋል።

የእዣ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሪት ረሂማ ሙህታጅ በወረዳዉ በሳይንሱ ዘርፍ በተለይ ትኩረት አድርገዉ እየሰሩ እንደሆነም አመላክተዋል።

በዞን ደረጃ በተዘጋጀዉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ዉድድር ጽህፈት ቤታቸዉ የዋንጫ ተሸላሚና አንደኛ እንደወጡም ተናግረዉ የተሸለሙት በቀጣይ የተሻለ ስራ መስራት እንደሚያነሳሳቸዉም ተናግረዋል።

ሌላኞዉ ከወልቂጤ ከተማ የግል ተወዳዳሪ ኢኖቬተር ይድነቃቸዉ ተክሉ አዉቶማቲክ የእሳት አደጋ መቆጣጠሪያ ለዉድድር ይዞ በመቅረብ አንደኛ እንደወጣና የዋንጫ ፣የገንዘብና የሰርተፍኬት ተሸላሚ መሆኑም ተናግሯል።

ይህ አዉቶማቲክ የእሰሳት አደጋ መከላከያ ቴከኖሎጂ ለመስራት ያነሳሳዉ በሀገራችን በተለያዩ የበአላት ወቅቶች የሚፈጠሩ የእሳት አደጋዎች በተለይም በአዲስ አበባ ባለፉት ሶስት ወራት በእሳት አደጋ እስከ 90 ሚሊየን ብር የመገመት ንብረት መዉደሙም አስታዉሶ ፈጠራዉም ይህንኑም ለማስቀረት እንደሆነም ተናግሯል።

ከዚህ ቀደም የእንጀራ መጋገሪያ ቴክኖሎጂ በማቅረብ አንደኛ ወጥቶ እስካሁን ይህ ቴክኖሎጂ ወደ ምርት እንዳልገባና የሚያግዘዉ ተቋምና ባለሀብት ማግኘት እንዳልቻለም ተናግሯል።

በመጨረሻም በአምስቱም ዘርፍ ከአንድ እስከ ሶስት የወጡ ተወዳዳሪዎችና የየወረዳና ከተማ አስተዳድር ጽህፈት ቤቶችና መምህራኖች የሰርተፍኬት ፣ የሜዳሊያና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *