የማህበረሰቡን የመተሳሰብ፣ የመደጋገፍና ተካፍሎ የመብላት እሴቱን ይበልጥ በማጎልበት አቅመ ደካማና ጧሪና ደጋፊ የሌላቸው ወገኖች በመደገፍ በዓሉ ማክበር እንዳለባቸው የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳደር አት ላጫ ጋሩማ አሳሰቡ።

ማህበረሰቡን የመተሳሰብ፣ የመደጋገፍና ተካፍሎ የመብላት እሴቱን ይበልጥ በማጎልበት አቅመ ደካማና ጧሪና ደጋፊ የሌላቸው ወገኖች በመደገፍ በዓሉ ማክበር እንዳለባቸው የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳደር አት ላጫ ጋሩማ አሳሰቡ።

የገና በዓል ምክንያት በማድረግ ከ120 በላይ ለሚሆኑ ተፈናቃዮችና ድጋፍ ለሚሹ አካላት የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ ማጋራቱን የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በማዕድ ማጋራቱ ላይ ተገኝተው እንደገለጹት የጉራጌ ማህበረሰብ መተሳሰብ፣ መተጋገዝና ተካፍሎ መብላት የቆየ ባህሉ መሆኑን ጠቅሰው አሁን ላይ እየተረሳና እየቀዘቀዘ መጥቷል።

ይህ የመደጋገፍና የመተሳሰብ ባህላችን በማጎልበት ማስቀጠል ይገባል ያሉት አቶ ላጫ ጧሪና ደጋፊ የሌላቸውና አቅም ለሌላቸው ወገኖች የመደገፍ ስራ መንግስት በትኩረት እየሰራ መሆኑ ገልጸው በዚህም ህብረተሰቡ መሳተፍ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

መሰል የመንግስትን በጎ ሃሳብ መነሻ በማድረግ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ጧሪና ደጋፊ ለሌላቸውና አቅመ ደካሞችን እንዲደግፉ ያሳሰቡ ሲሆን በዛሬው እለትም ማህበረሰቡ የመንግስትን በጎ ተግባር በመረዳት ወገኖቻቸውን እንዲረዱና እንዲደግፉ ለማነሳሳት በማሰብ ለተፈናቃይ ወገኖች የገና በዓል ምክንያት በማድረግ ማዕድ ማጋራት መቻሉንም ተናግረዋል።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሄኖክ አብልሰመድ በበኩላቸው የማዕድ ማጋራቱ በዓሉ ምክንያት በማድረግ ከ120 በላይ ለተፈናቀሉ ወገኖች ማዕድ ለማጋራት የዱቄት፣ የዘይትና የገንዘብ ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል።

የበጋ በጎፈቃድ አገልግሎት በመጠቀም ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ማዕድ በማጋራት በዓሉ ደስተኛ ሆነው እንዲያከብሩ በማሰብ ነው ያሉት አቶ ሄኖክ በዞኑ በሁሉም መዋቅሮች መሰል ድጋፎች እየተደረጉ መሆኑንም ገልጸዋል።

የዞኑ ማህበረሰብ በበጎነት ስራ ይታወቃል ያሉት ኃላፊው ይህን ባህል በማጉላት ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ ጠቁመው ማህበረሰቡም በዓሉ ሲያከብሩ ከተቸገሩ ወገኖችን በመደጋገፍና አብሮ በማክበር እሴቱን ማስቀጠል እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

በዛሬው ማዕድ ማጋራት ላይ ግሎባል ፉድ ኮምፕሌክስ አብድልወኪል ግራኝ፣ የወልቂጤ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅና ቀይ መስቀል ኢትዮጵያ ላደረጉላቸው ድጋፍ አመስግነዋል።

በዛሬው እለት ድጋፍ የተደረገላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች እንዳሉት የገና በዓል ምክንያት በማድረግ በተደረገላቸው ድጋፍ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው ለድጋፉም ምስጋና አቅርበዋል።

መሰል ድጋፎች ከበዓል ባለፈ በሌሎችም ወቅቶች ድጋፉ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

በማዕድ ማጋራት ፕሮግራሙም የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አበራ ወንድሙ፣ የዞኑ የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገብረመስቀል በተገኙበት ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።

በተያያዘም በጉራጌ ዞን እምድብር ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የከተማው ከንቲባ አቶ ግንባሩ በርጋ በተገኙበት ድጋፍ ተደርጎላቸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *