የማህበረሰቡን ችግር ለመቅረፍ እየተሰሩ ያሉ አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን ወደ ምርት በመቀየር የፈጠራ ባለቤቶች ለማበረታታት መስራት እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጃ መምሪያ አስታወቀ።


መምሪያው በተማሪዎች የተሰሩ የተለያዩ የፈጠራ ስራዎች በመምሪያው ስልጠና እየወሰዱ ላሉ ሰልጣኞች አስጎብኝቷል።

የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጃ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ እንደተናገሩት በዞኑ በፈጠራ ስራ የተሰማሩ በርካታ ተማሪዎች የሚገኙ ሲሆን እነዚህም የፈጠራ ስራቸው ላይ ውጤታማ ድጋፍና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

በፈጠራ ስራ ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪዎች በመደበኛ ትምህርታቸው ላይ ተጽእኖ ሳያሳድርባቸው ጎን ለጎን እንዲያድኬዱ እየተደረገ ሲሆን የፈጠራ ስራ ያላቸው ተማሪዎች ከዞኑ አልፎ በአገር አቀፍ የፈጠራ ስራ ውድድር እንዲሳተፉ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
በመሆኑም በ2016 ዓ.ም 4 ተማሪዎች የፈጠሯቸው ስራዎች ችግር ፈለቀ በመሆናቸው ከግብርና፣ ከኢንሳ፣ ከስራና ክህሎት ሚኒስተር ጋር በጋራ እንዲሰሩ ግንኙነት መፈጠሩ አቶ ደምስ ገልጸዋል።

አክለውም በተማሪዎቹ የተሰሩ የፈጠራ ስራዎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባዘጋጀው የፈጠራ ስፖዚየም ስራቸው እንዲያቀርቡ መደረጉ ያስታወሱት ኃላፊው በክልሉና በሀገር ደረጃውን ተወዳዳሪና የተሻለ አፈጻጸም ያላቸው ተማሪዎች ቁጥር በየዞኑ እየተበራከተ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

በመሆኑም እነዚህ የፈጠራ ባለቤት የሆኑ ተማሪዎች እየገጠማቸው ያለው የበጀት፣የቁሳቁስና የድጋፍ ችግር ተቀርፎላቸው እራሳቸውና ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይሰራል ብለዋል።

አቶ ደምስ አክለውም ተማሪዎቹ የሰሩዋቸው የፈጠራ ስራዎች የአምሮ ንብረት ባለቤትነት እንዲሰጣቸው እየተሰራ ሲሆን ትምህርት ቤቶች የማህበረሰቡን ችግር የሚቀርፉ ቴክኖሎጂ ፈጣሪ ትውልድ ለማፍራት የሳይንስና ፈጠራ ክበባ እንዲጠናከሩ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል ።

ዘርፉን ውጤተማ ለማድረግ ኮሌጆች፣ትምህርት ቤቶች፣ቤተሰብ፣መምህራንና ሌሎች የበኩላቸው ድርሻ መወጣት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ተማሪ ሙሀጅር ካሚል በያበሩስ ወልቂጤ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ የ9ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን (smart home automation system) ቤታችን በስልክ መቆጣር የምንችልበት የፈጠራ ስራ መስራቱን አስታውቋል።

ተማሪ ፍጹም ወርቁ ደግሞ በህዳሴ ፍሬ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪ ነው።
ተመሪው 20 የፈጠራ ስራዎች ያሉት ሲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ እውቅና ያገኘበትን በአንድ ሰዓት እስከ 9 መቶ የሆቴል ተስተናጋጆች የሚያስተናግድ ሮቦት ሰርቶ ለእይታ አብቅቷል።

ተማሪዎቹ በጋራ በሰጡት ሀሳብ የህብረተሰቡ ችግር በዘላቂነት የሚቀርፉ ወጪና ጊዜ ቆጣቢዎች የሳይንስና የቴክኖሎጂ ስራዎችን ለመስራት ጥረታቸው አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *