የሚኒስትሮች ም/ቤት የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ለማድረግ የቀረበ ረቂቅ ፖሊሲን አፀደቀ

ነሐሴ28/2014 ዓ.ም

የሚኒስትሮች ም/ቤት የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ለማድረግ የቀረበ ረቂቅ ፖሊሲን አፀደቀ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ለማድረግ በቀረበ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ተወያይቶ በሥራ ላይ እንዲውል ወሰነ።

የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ማድረግ የዘርፉን አገልግሎቶች በእውቀት እና በቴክኖሎጂ ለመደገፍ፣ የአገራችን ኢኮኖሚ ከዓለም አቀፍ ገበያ ጋር ያለውን ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር፣ የፋይናንስ ዘርፉን ተወዳዳሪነት፣ ውጤታማነትና ቀልጣፋነት በመጨመር በቂ የፋይናንስ አቅርቦት እንዲኖር የሚያስችል ረቂቅ ፖሊሲ በዛሬው ዕለት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡

ረቂቅ ፖሊሲው የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት እንዲሳለጥ፣ የሚፈጠረው የሥራ ዕድል እንዲጎለብት፣ ኢኮኖሚያዊ ውጤታማነትን እና ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪትን በማረጋገጥ ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑም ተመልክቷል።

በዚህም ምክር ቤቱ በፖሊሲው ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በሥራ ላይ እንዲውል መወሰኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ዘገባው ኤፍ ቢ ሲ ነው

እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Twitter:- https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *