የመንግስት ተቋማት ወጥ የሆነ የአሰራር ስርአትን በመዘርጋት የአገልግሎት አሰጣጡ በማሻሻል ወቅቱን የሚመጥን ስራ መስራት እንዳለባቸው የጉራጌ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት መምሪያ አስታወቀ።

መምሪያው ለወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር ፅህፈት ቤት ኃላፊዎችና ለማኔጅመንት አባላት በህዝብ ክንፍ ልየታ፣ በሰው ሃብት ሶስትዮሽ አሰራር ስርዓት፣ በእውቅናና ሽልማት መመሪያ፣ በኢንስፔክሽን ማኑዋልና በአጫጭር ስልጠና አዘገጃጀት ዙሪያ በወልቂጤ ከተማ ስልጠና ሰጥቷል።

የጉራጌ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ዙልፋ አለዊ በስልጠናው ወቅት ተገኝተው እንዳሉት ስልጠናው በመንግስት ተቋማት ላይ የሚነሳውን የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ ወሳኝ ነው።

የአገልግሎት አሰጣጡ ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲደርስ ለመንግስት ተቋማት ወጥ የሆነ የአሰራር ስርአቶችን ቢወርድም ተፈፃሚ ከማድረግ አንፃር የሚስተዋሉ ክፍተቶና ዜጎች የሚያነሷቸው ቅሬታዎች እንዳሉ ኃላፊዋ ተናግረረው ችግሮቹን ለመፍታት እንዲቻል ለሴክተሩ ባለሙያዎችና አመራሮች እንዲሁም ለባለድርሻ አካላት የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና በተለያዩ ጊዜ እየተሰጠ ነው ብለዋል።

በዞኑ ባሉ ተቋማት ጥራት ያለው የሰው ሃይል እንዲፈጠር የሶስትዮሽ የአሰራር ስርአት በተለይም ፋይናንስ፣ ፐብሊክ ሰርቪስና ቀጣሪ መስሪያ ቤቶች ትክክለኛ የአሰራር ስርአት በመከተል መስራት አለባቸው ብለዋል። ይህም በቅጥር ወቅት የሚፈፀሙ ህገ ወጥነትን ለማስቀረት ሚናው ትልቅ እንደሆነም አስረድተዋል።

ተቋማት በእቅድ፣ በምዘና ሂደት በሪፖርት ግምገማ ወቅት ላይ የህዝብ ክንፍ በተገቢው በማሳተፍ መስራት እንዳለባቸውም አመላክተዋል።

የመረጃ ስርአቱ ጥራት ያለው እንዲሆን ከአይሲቲ ተቋም ጋር በተባበር መረጃዎችን ወደ ኤሌክትሮኒክስ ስርአት ለመቀየር በኮምፒውተር የታገዘ ስልጠና ተሰጥቷል ብለዋል።

የመንግስት ተቋማት ወጥ የሆነ የአሰራር ስርአትን በመዘርጋት የአገልግሎት አሰጣጣቸው በማሻሻል ወቅቱን የሚመጥን ስራ መስራት እንዳለባቸውም ኃላፊዋ ገልፀዋል።

የጉራጌ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት መምሪያ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ አቶ ተከተል ገዛኸኝ ስልጠናው ሲሰጡ እንደተናገሩት ህዝብ የሚያነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በተደራጀ መልኩ በተገቢው በማቀድ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ስልጠናው ትልቅ ሚና አለው ብለዋል።

በስልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ በመያዝ በቀጣይ ወደ ታችኛው መዋቅር በማውረድ እንዲተገብሩና እንዲያስተገብሩ ነው ብለዋል።

አቶ ደሳለኝ ደግፌ ከመስቃን ወረዳ ወይዘሮ ጤናዬ ሱራፌል ከወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የስልጠናው ተሳታፊ ሲሆኑ በጋራ በሰጡት አስተያየት ስልጠናው ወቅታዊና የሚያነቃቃ እንደነበር ገልፀዋል።

በቀጣይም በስልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ በመያዝ ወደ መዋቅሮቻቸው በማውረድ ተፈፃሚ እንደሚያደርጉም ጠቁመዋል።

ተቋማት የህዝብ ክንፍን በአግባቡ በመለየትና በተገቢው በማሳተፍ ለህብረተሰቡ የተሻለና የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባም ተናግረው የ90 ቀናት እቅድ ተፈፃሚ እንዲሆን ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት አለበት ብለዋል።

በመጨረሻም በቀረቡ ሰነዶች ላይ ሰፍ ያለ ውይይት በማድረግ ከመድረኩ ምላሽ የተሰጠ ሲሆን የቀጣይ የዘጠና ቀን እቅድ የቀጣይ አቅጣጫ በማድረግ ስልጠናው ተጠናቋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ነው።

=ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *