የመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻልና ህዝቡ በየደረጃው የሚያነሳቸው የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት በትኩረት እየሰራ መሆኑ የጉራጌ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡

በባለፈዉ አንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ከመንግስት የስራ ሰዓት አከባበር፣ ስታንዳርድን ተከትሎ ተግባራትን መፈፀምና በህገ-ወጥ ቅጥር፣ ዝውውርና በደረጃ እድገት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች ለመቅረፍ በተሰራዉ ስራ ለዉጥ እየተመዘገበ እንደሆነም መምሪያው ገልፀዋል ።

መምሪያው ህዝብ የሚነሳቸዉን የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች ለመፍታት የ90 ቀናት እቅድ አቅዶ እየሰራ ነዉ።

የጉራጌ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ሀላፊ ወይዘሮ ዙልፋ አለዊ እንዳሉት በተቋሙ የ90 ቀናት እቅድ ውስጥ በዋናነት ትኩረት የተሰጠው ከአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ታቅዶ እየተሰራ እንደሆነም ጠቁመው ባለፈው አንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ከመንግስት የስራ ሰዓት አከባበር፣ ስታንዳርድን ተከትሎ ተግባራትን መፈፀምና ህገ-ወጥ ቅጥር፣ ዝውውርና የደረጃ እድገት በከፊልና ሙሉ በሙሉ ከተፈቱት መካከል ተጠቃሾች ናቸዉ፡፡

በየደረጃው ባሉ የመንግስት ተቋማት ባለሙያ በተገቢው በስራዉ ገበታዉ ላይ ተገኝቶ በቅንነት ከማገልገል አንፃር እና ተግባራትን በስታንዳርድ መሰረት መፈፀምና ስታንዳርድ የሌላቸውን ተግባራት ስታንዳርድ እንዲወጣላቸው መደረጉም አስረድተዉ የሚፀድቁ ህገ-ወጥ ቅጥር፣ የደረጃ እድገትና የዝውውር ችግሮችን ለመከላከል እንዲሁም የሰው ሀይል የማሟላት ስርአቱ የሶስትዮሽ የአሰራር ስርዓትን እንዲከተል ለሰው ሀብት ስራ አመራሮች ስልጠና መስጠታቸዉም አስታዉሰዋል።

እስካሁን ህገ-ወጥ ቅጥር ላይ በተደረገ ቁጥጥር በተሰራው ስራ ወደ 52 ሺህ ብር የተገኘ ሲሆን በዞን መምሪያ ደረጃ ለየሴክተሮቹ ግብረ-መልስ የተሰጠ ሲሆን ገንዘቡም እንዲመለስ ከቋሚ ኮሚቴው ጋር ትስስር በመፍጠር እየሰሩ መሆኑ ጠቁመዋል፡፡

መምሪያዉ በ90 ቀናት ዉስጥ ያቀዳቸዉን ተግባራት በቀሪ ጊዜ ዉስጥ ለማሳካት ቅንጅታዊ አሰራርን ተፈጥሮ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነም አስታዉቀዋል።

በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ጉድለቶችን ለማረምና የተገልጋይ ቅሬታን ለመቀነስ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ለአመራሩ፣ ለባለሙያውና ለባለድርሻ አካላት ስልጠና ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆናቸዉም አመላክተዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *