የመንግስት ተቋማት አካባቢያቸውን በችግኝ በማስዋብ ለሰራተኞችና ለተገልጋዮች ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር እንዳለባቸው በጂ. ኤንድ. ፒ. አካባቢ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ተናገሩ።

የተቋማቱ አመራሮችና ሰራተኞቹ የአረንጓዴ አሻራቸውን በተቋሞቻቸው ግቢ አኑረዋል።

የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራሙ አስተባባሪና የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ መሰረት አመርጋ የአረንጓዴ አሻራ የተስተካከለ የአየር ንብረት እንዲኖር ከማድረግ ባሻገር የተቋማቱ አካባቢ በአረንጓዴ ተክሎች ማስዋብ ይገባል ብለዋል።

እንደ ኃላፊዋ ገለጻ ተቋማቱ በአረንጓዴ ተክሎች ማስዋብ አካባቢው ነፋሻማና ማራኪ እንዲሆን በማድረግ ተገልጋዮች ጉዳዮቻቸው እስኪያስፈጽሙ ተረጋግተው እንዲጠብቁ ያስችላቸዋል።

በመሆኑም በጂ ኤንድ ፒ አካባቢ የሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤት አመራሮችና ሰራተኞች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች በመስሪያቤቶቻቸው ግቢ ተክለዋል ብለዋል።

የተቋማቱ ሰራተኞች የተተከሉ ችግኞች እንዲጸድቁ ውኃ ማጠጣት ፣ መኮትኮትና አካባቢው ከሰውና ከእንስሳት ንኪኪ ነጻ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል ።

በአረንጓዴ አሻራ የተሳተፉ የመንግስት ሰራተኞች በሰጡት አስተያየት የመንግስት ተቋማት አካባቢያቸውን በአረንጓዴ ችግኞች በማስዋብ ለሰራተኞችና ለተገልጋዮች ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

የተተከሉ ችግኞች እንዲጸድቁ በማድረግ ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር የራሳቸው አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ተናግረዋል።

የአረንጓዴ አሻራ ማኖር የአካባቢን ስነምህዳር እንዲጠበቅ ከማድረጉም ባለፈ የመንግስት ሰራተኞች የእርስ በርስ ግንኙነት እንዲጠናከር የራሱ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *