የመንግስት ሰራተኞች ለህብረተሰቡ የተሻለና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡ ምቹ የስራ አከባቢ መፍጠር እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።

የጉራጌ ዞን አስተዳደር በ11 ሚሊየን ብር ወጪ ለመንግስት ሰራተኞች የሰርቪስ አገልግሎት የሚውሉ ሁለት ባሶች ግዢ በመፈፀም ዛሬ ከጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር ርክክብ አደረገ።

የጉራጌ ዞን አስተዳደር ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሰፋ አካሉ በርክክቡ ወቅት እንዳሉት ፐብሊክ ሰርቫንቱ አገልግሎት በሚሰጥበት ተቋምና በተመረቀበት ዘርፍ የተሻለ አገልግሎት ለማህበረሰቡ እንዲሰጥ ምቹ የሆነ የስራ አከባቢ መፍጠር ያስፈልጋል።

የዞኑ መንግስት ሰራተኞች የበርካታ አመታት ጥያቄ የነበረው የሰርቪስ ጥያቄ በተለይም ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተያይዞ ጥያቄው እየጎላ መምጣቱን ጠቁመው የዞኑ አስተዳደር ከጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር ጋር በመተባበር ለፐብሊክ ሰርቫንቱ አገልግሎት የሚሰጡ ባሶቹ ግዢ ተፈፅመዋል ብለዋል።

ፐብሊክ ሰርቫንቱ ቀደም ሲል ከነበረው የስራ ባህል በተሻለ ሁኔታ አገለረግሎት መስጠት አለበት ያሉት አቶ አሰፋ መንግስትም በቀጣይ ከሲቪል ሰርቫንቱ ጎን በመቆም ህብረተሰቡ የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኝ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር ዋና ዳይሬክተር አቶ ቅባቱ ተሰማ እንደገለፁት ልማት ማህበሩ የዞኑ ህዝብ የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኝ ከዚህ በፊት ለዞኑ፣ ለወረዳና ለከተማ አስተዳደሮች ከ40 በላይ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ግዢ በመፈፀም ማቅረቡን አስታውሰው ማህበሩ በዞኑ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።

የዞኑ አስተዳደር ለበርካታ አመታ ባሶቹ ግዢ ለመፈፀም ጥረት እያደረገ እንደነበር አስታውሰው ለልማት ማህበሩ ከዞኑ አስተዳር በመተባበር ለፐብሊክ ሰርቫንቱ የሰርቪስ አገልግሎት የሚውሉ ሁለት ታታ ባሶችን በ11 ሚሊየን ብር ወጪ በአጭር ጊዜ ግዢ መፈፀሙንና ይህም ፐብሊክ ሰርቫንቱ የተሻለና የተቀላጠፈ አገልግሎት ለህብረተሰቡ እንዲሰጡ ያስችላቸዋል ብለዋል።

በቀጣይም ልማት ማህበሩ ሲቪል ሰርቫንቱና መንግስት ውጤታማ የሆነ ስራዎችን በመስራት ህብረተሰቡ ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኝ እየሰራ ያለው ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀም አመላክተዋል።

በዞኑ ልማት ማህበሩ የጀመራቸውን የልማት ስራዎችን መኖሩን ገልፀው ሲቪል ሰርቫንቱ ከልማት ማህበሩ ጎን በመቆምና በመደገፍ ልማት ማህበሩ ጠንካራ ድርጅት እንዲሆን የመንግስት ሰራተኛው እያደረገው ያለው እገዛ አጠናክሮ እንዲቀጠል ጠይቀዋል።

የጉራጌ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ዙልፋ አለዊ በበኩላቸው የፐብሊክ ሰርቫንቱ ጥያቄ ለመመለስ መምሪያው ከ2011 አመተ ምህረት ጀምሮ የባሶቹ ግዢ ለመፈፀም በርካታ ተግዳሮት እንደገጠመው ገልፀው ይህም በአጭር ጊዜ ተፈፃሚ እንዲሆን የጉራጌ ዞን አስተዳደር፣ የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር እና የዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ላደረጉት አስተዋፅኦ አመስግነዋል።

በተለይም ከዚህ በፊት ፐብሊክ ሰርቫንቱ በወር ያወጡት የነበረውን የባጃጅ ትራንስፖርት ውጪ ይቀርፋል ያሉት ኃላፊዋ ይህም ፐብሊክ ሰርቫንቱ ወደ ስራ ገበታቸው በጊዜ በመግባት የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ ባሶቹ ትልቅ ፋይዳ አላቸው ብለዋል።

አክለውም የፐብሊክ ሰርቫንቱ አቅም ለማሳደግ ምቹ የስራ ቦታ በመፍጠር በአገልግሎት የተማረረው ህብረተሰብ የተሻለና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ መምሪያው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እንደሚሰራም ጠቁመዋል።

ወይዘሮ መችበዙ ገብሬና አቶ ታደለ ትግስቱ በጋራ በሰጡት አስተያየት የፐብሊክ ሰርቫንቱ ችግር በመረዳት የዞኑ አስተዳደርና የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበሩ ለሰርቪስ አገልግሎት የሚውሉ ባሶች ግዢ በመፈፀሙ ትልቅ ደስታ እንደፈጠረባቸውም ተናግረዋል።

በተለይም ፐብሊክ ሰርቫንቱ ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ በትራንስፖርት ወጪ እየተማረረ እንደነበር ገልፀው የሲቪል ሰርቫንቱ ችግር በዚህ ልክ በመረዳት ለመቅረፍ ከፍተኛ ጥረት ላደረጉ ለዞኑ አስተዳደር፣ ለጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር እና ለመምሪያው አመስግነዋል።

ፐብሊክ ሰርቫንቱ በስራ ገበታው በጊዜ በመገኘት ለማህበረሰቡ የተሻለና ወቅቱን የሚመጥን አገልግሎት ለመስጠት መነሳሳት እንደሚፈጥረበት ተናግረዋል ሲል የዘገው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽንጉዳዮች መምሪያ ነው።

=ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *