የመስቀል በዓል የደመራ ስነ-ስርዓት በምሁር አክሊል ወረዳ በሚገኙ አድባራት በድምቀት እየበራ ነው።

መስከረም 16/2015ዓ.ም።


የመስቀል በዓል የደመራ ስነ-ስርዓት በምሁር አክሊል ወረዳ በሚገኙ አድባራት በድምቀት እየበራ ነው።

የመስቀል በዓል ከአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን (327 ዓ.ም) ጀምሮ እንደሚከበር ይነገራል፡፡ በዓሉ ሃይማኖታዊ ትውፊት ያለው በዓል ሲሆን አጀማመሩ የክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል ከመገኘት ጋር ተያይዞ የተጀመረ ዓመታዊ ክብረ በዓል ነው። የኢትዮጵያ ብሄር ብሄርሰብ በዓሉን የሚያከብረው እንደ ህዝቡ ባህል፣ ኣኗኗር፣ ወግ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ገጽታ ነው፡፡

በዘመኑ የነበረችው ንግሥት እሌኒ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል አስቆፍራ ካስወጣችበት ጊዜ ጀምሮ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ይከበራል፡፡ ንግሥቲቱ መስቀሉ የተቀበረበትን ቦታ ኪራኮስ በተባሉ አባት ጠቋሚነት ለማግኘት ደመራ አስደምራ ፍለጋ የጀመረችው መስከረም 17 ቀን እንደሆነ የክርስትና ሃይማኖት ድርሳናትና የሃይማኖት አባቶች ያወሳሉ፡፡

መስቀሉን ለማግኘት የሃይማኖት አባቶችን አሰባስባ በፀሎት እንዲረዷት ጠይቃ፤ ከደመራው በሚወጣው ጢስ ጠቋሚነት መስቀሉ የተቀበረበትን ቦታ አግኝታለች፡፡

መስቀሉም ከወራት ፍለጋና ቁፋሮ በኋላ መጋቢት 10 ቀን መውጣቱን ተከትሎ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እንደ ሃገር መስከረም 16 ቀን ‹ደመራ› እና መስከረም 17 ቀን ‹የመስቀል በዓል› እየተባለ ይከበራል።

የደመራ ስነ-ስረዓቱ መስከረም 16 የሚከበር ሲሆን በምሁር አክሊል ወረዳ በሚገኙ ቤተ-ክርስትያኖች ሓይማኖታዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ እንዲህ ተከብሯል ሲል የዘገበው የምሁር አክሊል ወረዳ የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

መልካም የደመራ በዓል!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *