የመስቀል በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ የቡታጅራ ከተማ ፖሊስ አባላት ከማህበረሰቡና ከወጣቶች ጋር በመቀናጀት በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ!!

መስከረም 13/2015 ዓ.ም

የመስቀል በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ የቡታጅራ ከተማ ፖሊስ አባላት ከማህበረሰቡና ከወጣቶች ጋር በመቀናጀት በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ!!

የመስቀል በዓል ሀገራችን ላይ ብሎም እንደ ጉራጌ ማህበረሰብ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው በዓል እንደመሆኑ የጉራጌ ልጆችና ባለሀብቶች በዓሉን ለማክበር ከተለያዩ የሀገሪቷ ክፍል ወደ ቀያቸው እየገቡ ሲሆን ቡታጅራ ከተማም ልጆቿን ሽር ጉድ እያለች በመቀበል ላይ ትገገኛለች።

የቡታጅራ ከተማ ፖሊስ ከከተማው ህብረተሰብና ከበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ጋር በመሆን ከተማዋ ከትራፊክ መጨናነቅ ነፃ እንድትሆን እንግዶችንም በሰላም ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲገቡ በቅንጅት የማስተናበር ስራ እየተሰራ እንደሆነ ፖሊስ ገልጿል።

የቡታጅራ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ሙሰማ ጀማል እንደገለፁት ቡታጅራ ከተማ በዓራቱም አቅጣጫ መግቢያና መውጫ በሮች ያሏት ከተማ እንደመሆኗ የጉራጌ ተወላጆችና ባለሀብቶች በዓሉን ለማክበር ወደ ቤተሰቦቻቸውና ወደ ትውልድ ቀያቸው ሲገቡ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይኖርና የከተማዋ ሰላም አስተማማኝ እንዲሆን ፖሊስ ከከተማው የበጎ ፍቃድ ወጣቶችና ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን ከቀደም ብለው ውይይት በማድረግ ሰፊ ዝግጅት ተደርጎ ወደ ስራ በመገባቱ ውጤታማ ስራ እየሰሩ እንደሆነ ተናግረዋል።

አዛዡ አክለውም በዓልን ምክንያት በማድረግ በገበያ አካባቢ ሀሰተኛ የብር ኖቶች በመያዝ የሚያጭበረብሩ እና በባንኮች አካባቢ የተለያዩ የስርቆት መንገዶችን በመጠቀም የሚሰርቁ አካላት እንዲሁም በተለያዩ ምርቶች ላይ በተለይ በቂቤ ፣ በበርበሬ እና በዱቄት ምርቶች ላይ በዓድ ነገሮችን ጨምረው የሚሽጡ ስግብግብ አካላት ሊኖሩ ስለሚችል ህብረተሰቡ የትኛውንም ምርት ሲገዛም ሆነ ሲሸጥ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል።

በዓሉን በሰላም እንዲጠናቀቅ የከተማው ህብረተሰብ እንደወትሮ ከፖሊስ ጋር በመሆን አካባቢው ላይ የትኛውንም አጠራጣሪ ጉዳዮችን ሲመለከት ከታች በተጠቀሱ ስ.ቁ.ላይ ጥቆማ እንዲደርጉ የከተማው ፖሊስ ጥሪ አስተላልፈዋል።

  • * ** *
    የቡታጅራ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ስ.ቁ 0461151322 ወይም ከተማ ፖሊስ ሞባይል ቀጥር +251930887677 መሆኑን የከተማው ኮሚዩኒኬሽን አድርሶናል።

ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *