የመስቀል በአል ሀይማኖታዊና ባህላዊ ይዘቱን ተጠብቆ እንዲከበርና በሰላም ያለምንም የጸጥታ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የበኩሉን መወጣት እንዳለበት ተገለጸ።

መስከረም 14 /2015 ዓ.ም

የመስቀል በአል ሀይማኖታዊና ባህላዊ ይዘቱን ተጠብቆ እንዲከበርና በሰላም ያለምንም የጸጥታ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የበኩሉን መወጣት እንዳለበት ተገለጸ።

የጉራጌ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ እና የዞኑ ፖሊስ መምሪያ በጋራ በመሆን የመስቀል በአል አስመልክተዉ መግለጫ ሰጥተዋል።

መምሪያዎቹሁ ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለመስቀል በአል በሰላም አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

የጉራጌ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ተወካይ እና የሚሊሻ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብድልሀፊዝ ሁሴን በአሉን አስመልክተዉ በሰጡት መግለጫ የመስቀል በአል በሰላም እንዲጠናቀቅ ከዝግጅት ምዕራፍ እስከ ማጠቃለያዉ ድረስ እቅድ ታቅዶ እየተሰራ ሲሆን በዚህም ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ጋር ዉይይት ተደርጎ ወደ ተግባር ተገብቷል።

አሁን ላይ ዞኑ በኮማንድ ፓስት ስር ሲሆን ከዞኑ ሰላምና ጸጥታ መምሪያና ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በተገቢዉ መድረክ በመፍጠርና ይህንንም መድረክ ነታችኛዉ መዋቅር በአሉ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

የመስቀል በአል ሀይማኖታዊና ባህላዊ ይዘቱን ተጠብቆ እንዲከበርና በሰላም ያለምንም የጸጥታ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የበኩሉን መወጣት አለበት ብለዋል።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ጠጄ መሃመድ በበኩላቸው የ2015 የመስቀል በዓል ሠላማዊ እንዲሆን ለሁሉም የፀጥታ አካላት ወቅታዊና በቂ ግንዛቤ መፈጠሩን ገልፀው ህብረተሰቡም በተለይ ፀጉረ ልውጦችን በማጋለጥና ሌሎች ሠላምን የሚያውኩ ተግባራትን በመከላከል ለፀጥታ መከበር ውጤታማነት ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ አሳስበዋል ።

የአደረጃጀትና መሠል ጥያቄዎችን ምክንያት በማድረግ አላስፈላጊና የተከለከሉ ህገ ወጥ ተግባራትን ከማከናወን ሁሉም አካላት ሊታቀቡ ይገባል ያሉት ኮማንደሩ በተለይ በተለያዩ ስፍራዎች ፅሁፎችን መፃፍ፣ ባነር መለጠፍና መሠል ተግባራትን ማከናወን በህግ የሚያስጠይቁ ናቸው ብለዋል።

የአካባቢውን ሠላም ለማስከበርና መልካም ገፅታን ለመገንባት የወጣቶች ሚና ከፍተኛ ነው ያሉት ኮማንደር ጠጄ በመሆኑም ወጣቱ ከስሜታዊነት መንፈስ ተላቆ ራሱን ከእኩይ ተግባራት በማራቅና ህገ ወጥ ድርጊቶችን በመቆጣጠር ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

የመስቀል በዓል አከባበር በዩኒስኮ ከተመዘገቡ የማይዳሰሱ ቅርሶች አንዱ እንደሆነ የተናገሩት አዛዡ በመሆኑም የበአሉን መልካም እሴት ሊጎዱ ከሚችሉ ተግባራት በመታቀብ ማክበር ይገባል ብለዋል።

በበአሉ ወቅት የህብረተሰብ ማህበራዊ መስተጋብርና ግብይቶች ከሌላ ጊዜ በተለየ መልኩ የሚጠናከርበት በመሆኑ ይህንን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም በገበያ ስፍራዎችና የንግድ ማእከላት ሊፈፀሙ ከሚችሉ የማጭበርበር ወንጀሎች ህብረተሰቡ እንዲጠነቀቅም አሳስበዋል።

ከዚህም ባለፈ ሊያጋጥሙ ከሚችሉ የእሳትና መሠል አደጋዎች ራስንና አካባቢን በመጠበቅ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ የሚደርሰውን አደጋ መከላከል ያስፈልጋል ብለዋል።

ማናቸኛውም ለሚፈጠሩ የፀጥታ ቸግሮችና አደጋዎች የዞኑ ፓሊስ መምሪያ በ0113300323 በመደወል መረጃ መስጠት እንደሚቻል ገልፀዋል።

በመጨረሻም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለመስቀል በአል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን ሀላፊዎቹ በመግለጫቸው አስተላልፈዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *