የመሬት አስተዳደር ስርዓት በህግ አግባብ በመምራት አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

መምሪያው በመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም፣በመሬት ህግ አተገባበር መሰረታዊ የህግ ማእቀፎች እንዲሁም በመሬት አጠቃቀም መሰረታዊ የአሰራር ቅደም ተከተል ዙሪያ ለባለድርሻ ኣካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በወልቂጤ ከተማ መሰጠቱን ተመልክቷል ።

ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ አበራ ወንድሙ ስልጠናው በገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅና ደምብ ላይ የሰፈሩትን ድንጋጌዎች ወደ ተግባር ለማሸጋገር እንዲሁም ጎጂ የመሬት አጠቃቀም ተግባራትን ለመቆጣጠር ያስችላል ብለዋል።

የዘርፉ አመራርና ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት የመሬት እንክብካቤ ተግባራትን በመለየትና በመተግበር እንዲሁም በመሬት ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ጎጂ አጠቃቀሞችን መለየትና መቆጣጠር እንደሚያስፈልግ አቶ አበራ ገልጸዋል።

አመራሩ የመሬት ሀብታችን በባለቤትነትና ወቅቱን በሚመጥን ደረጃ መምራት ያስፈልጋል የሚሉት አቶ አበራ የመሬት መረጃ አያያዝን ወደ ዘመናዊነት ከመቀየር ኣንጻር ሰፊ ስራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ መኪ ሀሰን በበኩላቸው ከገጠር መሬት አጠቃቀም አንጻር ማሳዎች ተለክተው ለአርሶ አደሩ የባለቤትነት ደብተር ተዘጋጅቶ ከማስተላለፍ ኣንጻር ያለውን ክፍተት ለመሙላት ከባለድርሻ ኣካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል።

የህብረተሰቡን ኑሮ ለማሻሻልና ከድህነት ለማላቀቅ በየደረጃው የሚደረጉ የልማት ተግባራት በመሬት አስተዳደር ላይ የራሱን አሻራ ማሳረፍ እንዳለበት አቶ መኪ አክለው ገልጸዋል።

አቶ ብርሀኑ በቀለ በመምሪያው የመሬት አጠቃቀም ባለሙያ ሲሆኑ አግባብ ባልሆነ የመሬት አጠቃቀም ሳቢያ የመሬት መጎሳቆልንና የአየር ንብረት መዛባትን ለመከላከል ኣሳታፊ የቀበሌ መሬት አጠቃቀም ስርአትን መተግበር ያስፈልጋል ብለዋል።

አክለውም አቶ ብርሀኑ በወል መሬቶች ላይ የሚስተዋለው የባለቤትነት ችግር ለመቅረፍ መሬት የመንግስትና የህዝብ ሀብት እንዲሆንና ግለሰቦች የገጠር መሬት ባለይዞታና ተጠቃሚ የሚሆኑበት ህገ መንግስታዊ የአሰራር ስርአት ተዘርግቷል ብለዋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው መሬት የመልካም አስተዳደር ችግር መነሻ ጭምር ሊሆን ስለሚችል በአግባቡና በእውቀት መመራት እንዳለበት ገልጸዋል።

የህግ ማእቀፍና የአሰራር ስርአት በመዘርጋት በየደረጃው የሚፈጸሙ የመሬት ወረራና ቅርምት ለመከላከል በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል

ተሳታፊዎቹ አክለውም በስልጠናው የአዋጅ ጥሰትንና የአሰራር ክፍተቶችን በመድፈን ወጥ የሆነ ተቋማዊ አሰራርን በመዘርጋት ችግሩን ለመቅረፍ የሚያስችል ግንዛቤ እንዳገኙ ገልጸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዘግቧል።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

=ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *