የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህላዊ እሴቶችን በማጠናከር ለተለያዩ ችግር የተጋለጡ የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖች በአረፋ በአል ተደስተዉ እንዲዉሉ ማድረግ እንደሚገባም የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ።

የአረፋን በዓል ምክንያት በማድረግ በተደረገላቸዉ ድጋፍ መደሰታቸዉ በምስራቅ መስቃን የኢንሴኖ ከተማና በማረቆ ወረዳ ቆሼ ከተማ ድጋፍ የተደረገላቸዉ የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖች ገለጹ።

ለ1ሺህ 4 መቶ 44ኛ ጊዜ የሚከበረዉ የኢድ አል አደሃ አረፋ በአል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ።

የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ መሰረት አመርጋ እንዳሉት የአረፋ በአል ከእስልምና እምነት ተከታዮች ባለፈ የሌሎችም እምነት ተከታይ የህብረተሰብ ክፍሎች በፍቅርና በጉጉት የሚጠብቀዉ በአል ነዉ።

በዞኑ ማህበረሰብ ዘንድ የአረፋ በአል በልዩ አካባበር የሚከበር ሲሆን በተለይ ተራርቀዉ የነበሩ የእምነቱ ተከታይ ወገኖች ቤተሰቦቻቸዉናን ዘመድ ፣ጓደኛ የሚያገኙበትም ጭምር እንደሆነም አመላክተዋል።

በአሉ በጋራ በአብሮነት የሚከበር ሲሆን በአሉም አቅም የሌላቸዉ ለእምነቱ ተከታይ ወገኖች ማዕድ የማጋራት ፣አልባሳት የሚለግሱበት የሚደገፉበት እንደሆነም ጠቅሰዉ በአሉም ከሌሎች እምነት ተከታይ ወገኖች ጋር በአብሮነት የሚያከብሩበት እንደሆነም አብራርተዋል።

የሌሎች እምነት ተከታይ የህብረተሰብ ክፍሎች ፣ ከእንሰት ዝግጅት ጀምሮ በቤት ማስዋብ በጎመን ክትፎና በሌሎችም ስራዎች ላይ ሚያግዙበት እንደሆነም ተናግረዉ ይህም ማህበራዊ መስተጋብሩ ለየት የሚያደርገዉ ነዉ ብለዋል።

ኢትዮጵያዉያን የተቸገሩ ወገኖች በመርዳት የሚታወቁ እንደሆነም ጠቅሰዉ ህዝበ ሙስሊሙ እንደከዚህ ቀደሙ የተቸገሩ ወገኖቾ የመርዳ ባህሉ የለጠ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል።

አንዱ ሲበላ ሌላዉ መቸገር የለበትም ያሉት ወይዘሮ መሰረት የቀየሩበት አልባሳት ለተቸገሩ ወገኖች መስጠት እንዳለባቸዉና ተቋማቸዉ ባህልን ከማስተዋወቅና ሀይማኖታዊ ይዘቱን ከመጠቅ ባለፈ የተቸገሩ ወገኖችን የመደገፍ ስራ ይሰራል ብለዉ ይህም የመረዳዳት ባህሉ የበለጠ ጠንካራ እንዲሆን ለማህበረሰቡ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየሰሩ እንደሆነም ተናግረዋል።

የእርስ በእርስ የመተጋገዝ ባህላችን ማዳበር እንዲኖር ከመቼዉም ጊዜ በላይ እየሰሩ እንደሆነም አብራርተዉ ተቋማቸዉ ከ50 ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ በኢንሴኖ ከተማ እና በማረቆ ወረዳ 30 ለሚሆኑ ለተለያዩ ችግር የተጋለጡ የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖች የአልባሳትና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች በአሉን ምክንት በማድረግ ድጋፍ ማድረጋቸዉም አብራርተዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸዉ የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖች በሰጡት አስተያየት ህዝበ ሙስሊሙ ከተቸገሩት ወገኖች ጋር በመሆን የአረፋ በአል አብሮ በማክበርና ያለዉን ተካፍሎ በመብላት የተለመደዉ የመረዳዳት ባህል ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።

የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ በአሉን ምክንያት በማድረግ ላደረገላቸዉ የአልባሳትና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ከፍተኛ ምስጋናም አቅርበዋለ ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *