የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህላችንን በማጎልበት በዞኑ የተጀመሩ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አሳሰቡ።

የደቡብ ክልል የብልጽግና ፓርቲ የስራ ኃላፊዎችና የዞኑ አስተዳዳሪና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት በቡታጅራ ከተማ የአረጋዊያን ቤት ግንባታ አስጀመሩ።

በበጋ በጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራ በመንግስትና በህብረተሰቡ ይወጣ የነበረውን ከ1መቶ 39 ሚሊዮን ብር በላይ በበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ማዳን ተችሏል።

በቤት ግንባታ ማስጀመር ስራ ላይ የተገኙት የደቡብ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ እንዳሉት የብልጽግና አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች ከፓርቲው እሳቤ የታቀዱ የመደመርና፣ የአንዱን ጉድለት በሌላው በመሸፈንና በመደጋገፍ የብልጽግና ጉዞ ማስቀጠል እንደሚገባ መክረዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ጀማል በበኩላቸው በዞኑ የበጎ አድራጎት ስራ ከጊዜ ወደ ጊዜ ባህል ተደርጎ እየተሰራበት እንደሆነ አመላክተው የተጀመረው የአረጋዊኑ ቤት ግንባታ ስራ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ ሙሉ ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።

የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህላችንን በማጎልበት በዞኑ የተጀመሩ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተግባሮቻችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም አሳስበዋል።

ዞኑ የጀመራቸውን አቅመ ደካሞችን የማገዝና የመደገፍ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመው ለአብነትም በጤና መድን ብቻ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉ አስገንዝበዋል ።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትል ሀላፊና የወጣት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱ ድንቁ እንዳሉት የበጎ አድራጎት ስራው ማህበረሰቡ በማሳተፍ በጋራ በመሆን ራሱ ማህበረሰቡን የሚጠቅሙ የተለያዩ የልማት ስራዎች እየተሰራ ነዉ።

በበጋ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራ 139 ሚሊዮን 712 ሺህ 8 መቶ 21 ብር በመንግስትና በህብረተሰቡ ይወጣ የነበረ ወጪ በበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ማዳን መቻሉም አስታውቀዋል።

አክለውም 4 መቶ 84 ቤቶች አዲስ በመገንባትና በመጠገን የይዞታ ማረጋገጫ የሌላቸው የይዞታ ማረጋገጫ በማሰራት ለአቅመ ደካሞች የማስተላለፍና ያልተጠናቀቁት የቤት ግንባታ ስራዎች የማጠናቀቅ ስራ እየተሰራ ይገኛል ያሉት አቶ አብዱ በበጋዉ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራ 165ሺ 8 መቶ 91 ወጣቶች ተሳታፊ ሲሆኑ 3መቶ 64ሺ 5 መቶ 12 የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ሆነዋል ብለዋል።

ወ/ሮ አሚና አሊ የቤት እድሳት የተደረገላቸው እናት ሲሆኑ ከገጠማቸው የጤና ችግር በተጨማሪ የቤታቸው ማፍሰስና የቤቱ መውደቅ ያሳስባቸዉ እንደነበረና ሁል ጊዜ በስጋት ይኖሩ እንደነበረም አስታዉሰዋል።

ዛሬ ይህን እድል አግኝተው ቤታቸው ሊሰራ በመሆኑ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልፀው ይህንንም ላደረገላቸው መንግስትና የአካባቢው በጎ አድራጊ ወጣቶች ምስጋና አቅርበዋል።

በመረሃ ግብሩ ላይ የደቡብ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወይዜሮ ፋጤ ሶርሞሎ፣የደቡብ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ፣የደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይለማሪያም ተስፋዬ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማልን ጨምሮ የክልል፣ የዞንና የልዩ ወረዳ ሰልጣኝ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው ።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *