የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በእንስሳት ዘርፍ ያለውን አቅም በመጠቀም የህብረተሠቡን ህይወት ለመቀየር ዕድል የሚሰጥ መሆኑን ተገለፀ።

ጥር 4/2015ዓ.ም

የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በእንስሳት ዘርፍ ያለውን አቅም በመጠቀም የህብረተሠቡን ህይወት ለመቀየር ዕድል የሚሰጥ መሆኑን ተገለፀ።
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በእንስሳት ዘርፍ ያለውን አቅም በመጠቀም የህብረተሠቡን ህይወት ለመቀየር ዕድል የሚሰጥ መሆኑን የምስራቅ መስቃን ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመዲን ደድገባ ገለፁ።

በምስራቅ መስቃን ወረዳ “ምግቤ ከጓሮዬ አመርታለሁ የተመጣጠነ ምግብ እመገባለሁ” በሚል መሪ ቃል ወረዳዊ የሌማት ትሩፋት መርሃግብር ተካሂዷል።

የምስራቅ መስቃን ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመዲን ደድገባ ተገኝተው መርሃ ግብሩን በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት የሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር የዜጎችን የምግብ መሶብ ከማሳ ጋር የሚያስተሳስር መሆኑን አብራርተዋል፡፡

እንዲሁም የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በእንስሳት ዘርፍ ያለውን አቅም በመጠቀም የህብረተሠቡን ህይወት ለመቀየር ዕድል የሚሰጥ መሆኑንም አያይዘው ተናግረዋል።

በአረንጓዴ አሻራ፣ በበጋ መስኖ፣ በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በሌሎች ዘርፍ የተገኘውን ስኬት በእንስሳት፣ በዶሮ እና በማር ምርት በመድገም የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባም የተናገሩ ሲሆን

የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ የተሳካ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባም ዋና አስተዳዳሪው አያይዘው ገልፀዋል።

የምስራቅ መስቃን ወረዳ ምክትል አስተዳደርና ግብርና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሻፊ ሁሴን በበኩላቸው መርሃ-ግብሩ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥና ስርዓተ ምግብን ከማሻሻል ባሻገር የኢኮኖሚ ሉዓላዊነቷን ያስከበረች ነጻ አገር እውን ለማድረግ መሰረት የሚጥል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር ግቡን እንዲመታ የተሻሻሉ የዶሮ እና የእንስሳት ዝርያዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም አቶ ሻፊ ተናግረዋል፡፡

በግብርና ፅ/ቤቱ ምክትል እና የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ነስረላ ነጋሽ እንዳሉትም መርሃ-ግብሩ አርሶ አደሮችንና አርብቶ አደሮችን የሚያገናኝ ድልድይ በመሆን የወረዳውና አካባቢው ህብረተሰብ የምግብ ፍላጎት ለማሟላት ይረዳልም ብለዋል።

በተጨማሪም የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እና ስርዓተ ምግብን ማሻሻል እንደዋነኛ ዓላማ የያዘ መርሃግብር መሆኑን በመግለፅ

በወረዳው የሌማት ትሩፋት ስኬታማ ለማድረግ የእንስሳት ዝርያ ማሻሻልና መኖ ልማት ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም በመርሀ ግብሩ ተገልጿል።

የመርሃ ግብሩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የሌማት ትሩፋት በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ የተመጣጠነ ምግብ በማቅረብ ጤናው የተጠበቀ አምራች የሰው ኃይል ለማፍራትና እንዲሁም

ወተት፣ ማር፣ ስጋ እና እንቁላል መሰል የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶችን በገበያ ላይ በቀላሉ ለማትረፍረፍ እና የሌማቱ በረከት ለማብዛትም አስተዋጽኦው የላቀ መሆኑን ተናግረዋል።

በመርሃ ግብሩ በወረዳው በዶበና ባቲ ቀበሌ ሞዴል አርሶ አደር ሙህዲን መኩሪያ ጓሮ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም የእንስሳትና የዶሮ እርባታ ተዋፅኦዎችን የተጎበኙ ሲሆን በጉብኝቱ የእንሴኖ ከተማ አስተዳደርና የወረዳው አመራሮች፣ የግብርና ፅ/ቤት ኃላፊዎች ፣ ሊቀመናብርቶችና ሌሎችም አካላቶች ተገኝተዋል ሲል የዘገበው የወረዳው መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *