የህጻናት የትምህርት ተሳትፎ እና ጥራት ማሳደግ ጊዜው አሁን ነው”በሚል መሪ ቃል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ሴቶችና ህጻናት ቢሮ የአፍሪካ የህጻናት ቀን በዓል በወልቂጤ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።


የህጻናት የትምህርት ተሳትፎ እና ጥራት ማሳደግ ጊዜው አሁን ነው”በሚል መሪ ቃል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ሴቶችና ህጻናት ቢሮ የአፍሪካ የህጻናት ቀን በዓል በወልቂጤ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።

ህብረተሰቡን በማስተባበር ከ1 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ሀብት በማሰባሰብ ለ31ሺ 6 መቶ 53 ህጻናት የትምህርት ቁሳቁስ እና ልዩ ልዩ ድጋፍ ማድረግ መቻሉን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህጻናት ቢሮ አስታወቀ።

የአፍሪካ የህጻናት ቀን በአፍሪካ ለ34ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ33ኛ ጊዜ የህጻናት የትምህርት ተሳትፎና ጥራት ማሳደግ ጊዜዉ አሁን ነዉ በሚል መሪ ቃል በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ሰርሞሎ እንዳሉት በየዓመቱ ሰኔ 9 ቀን የሚከበረው የአፍሪካ የህጻናት ቀን በዓል መነሻው በህጻናት ላይ ከደረሰው ጭቆና፣በደል እንዲሁም ኢ ፍትሀዊ አሰራር እና የመብት ጥሰት መነሻ እንደሆነም ተናግረዋል።

የህጻናትን መብት፣ደህንነት እና ፍላጎታቸውን ለማሟላት የሚካሔደውን እንቅስቃሴ በባለቤትነት መምራት እንደሚያስፈልግም አብራርተዋል።

የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የህጻናትን መብት ማካተት በሁሉም ደረጃ እውን እንዲሆን በ2030 የአፍሪካ ህጻናት ዘላቂ ደህንነት አቅም ግንባታ እኩል ተጠቃሚነት አጀንዳ በመቅረጽ በዓሉ እየተከበረ ነው ብለዋል።

በበዓሉ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ሴቶችና ህጻናት ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ባይዳ ሙንዲኖ እንዳሉት የአፍሪካ ህፃናት ቀን እ.አ.አ ሰኔ 16 ቀን 1976 በደቡብ አፍሪካ ስዌቶ ከተማ ውስጥ በተማሪዎችና ህጻናት በተከሰተው ኢ-ፍትሃዊ የትምህርት አሰጣጥና የአፓርታይድ ስርአትን መቃወምን ተከትሎ በአፓርታይድ ስርአቱ የተገደሉ ህፃናት ለማሰብና ለመዘከር የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት በየአመቱ ሰኔ (9) የአፍሪካ ህጻናት ቀን ሆኖ እንዲከበር በ1991 እ.አ.አ. መወሰኑ አስታዉሰዋል።

ሕፃናት ከጨቅላ ዕድሜያቸዉ ጀምሮ ልዩ እንክብካቤና ድጋፍ
የሚፈልጉ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደመሆናቸው መጠን የህጻናትን መብትና ግዴታ ማስጠበቅና የህጻናትን ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ደህንነት በተሟላ ማረጋገጥ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ቅድሚያ የሚሰጠዉ ተግባር ሊሆን እንደሚገባም ተናግረዋል።

በሕፃናት ላይ በርካታ የመብት ጥሰቶች የሚፈጸሙ ሲሆን እነዚህ የመብት ጥሰቶች አብዛኛው ማህበረሰቡ እያየና እየሰማ የሚፈጸሙ ሲሆን የመብት ጥሰቶቹ በአመዛኙ በሕፃናቱ የቅርብ ዘመዶች፤ ወላጆች፤ ሕጻናቱን እንዲጠብቁና እንዲያስተምሩ ኃላፊነት በተሰጣቸው ግለሰቦችና አካላት ጭምር የሚፈጸም አንደሆነም አመላክተዋል።

በአካባቢያችን፤ በቤታችን፤ በጎረቤቶቻችን ወዘተ የሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶች በመከላከል ሕጻናት በህይወት ኖረዉ ነገ በአእምሮና በአካል የዳበሩ ዜጎች ሆነዉ አድገው ለራሳቸው፤ ለማህበረሰባቸውና ለሀገር አድገትና ብልጽግና የበኩላቸዉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ማደረግ እንደሚገባም አስረድተዋል።

ህብረተሰቡን በማስተባበር ከ1 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ሀብት በማሰባሰብ ለ31ሺ 653 ህጻናት የትምህርት ቁሳቁስ እና ልዩ ልዩ ድጋፍ ማድረግ መቻሉን አስታዉሰዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ እንዳሉት የነገዉ ሀገር ተረካቢ ህጻናት ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠትና በጥሩ ስነ ምግባር ታንጸዉ እንዲያድጉ የሁሉም ሰዉ ሀላፊነት እንደሆነም አመላክተዋለ።

በእለቱም የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳደር ተወካይ አቶ ዳርጌ ተክሉ እንዳሉት መንግስት የዜጎችን ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ለማስከበር መልካም አስተዳደር ለማስፈን አጽኖት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነም ተናግረዋል።

የክልሉ ህጻናት ፓርላማ ዋና አፈ ጉባኤ ህጻን ተከተል ግርማ በበኩሉ ህጻናት በአካልና በአእምሮ ያልበቁ በመሆናቸዉ ድጋፍና እንክብካቤ ይሻሉ ብሏል።

በበዓሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ሰርሞሎ፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ኤርሲኖ አቡሬ ፣ የክልሉ ሴቶችና ህጻናት ቢሮ ሀላፊ ባይዳ ሙንዲኖና ሌሎችም የዞኑ ሴቶችና ህጻናት መምሪያ ሀላፊ ወይዘሮ ነጅቢያ መሀመድና ሌሎችም ባለድርሻ አካላቶች ተሳትፈዋል።

በመጨረሻም በክልሉ ለሚገኙ የሴቶችና ህጻናት መምሪያና ጽህፈት ቤቶች የእዉቅናና የምስክር ወረቀት እንዲሁም ለተለያዩ ችግር ተጋላጭ ለሆኑ ህጻናት የትምህርት ቁሳቁስና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጎላቸዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *