የህግ ታራሚዎች በእውቀትና በጥሩ ስነ ምግባር ታንፀው እንዲወጡ ለማድረግ የትምህርትና የተለያዩ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ገለፀ ።

በበጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ማህበረሰቡን የሚጠቅሙ የልማት ስራዎች እያከናወኑ መሆኑም ተጠቁሟል።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱ ድንቁ በወልቂጤ ከተማ ማረሚያ ተቋም ለሚገኙ ታራሚዎች የተለያዩ መጽሀፍትና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ ባደረጉበት ወቅት እንዳሉት በዞኑ የ2014 ዓመተ ምህረት በበጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማህበረሰቡን የሚጠቅሙ የተለያዩ የልማት ስራዎች በዞኑ በሁሉም አካባቢዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ከ50 በላይ ለሚሆኑ ታራሚዎች የሳሙና፣ የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ እንዲሁም የተለያዩ አጋዥ መፅሐፍት የትምህርት ቁሳቁሶ ድጋፍ ማድረጋቸዉም ገልፀዋል።

ዛሬ ላይ በተለያዩ ምክንያት የህግ ታራሚ የሆኑ ዜጎች በቆይታቸው በሚያገኟቸው በቀለም፣ በሞያና በተለያዩ እውቀቶች እራሳቸውን በማዳበር በጥሩ ስነ ምግባር ታነፀው ወጥተው ነገ የተሻለ አምራች ዜጋ እንዲሆኑ ለማስቻል ተቋሙ የተጣለበትን ድርሻ እንዲወጣ ለማስቻል ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ብለዋል ።

አክለዉም አቶ አብዱ ድንቁ የህግ ታራሚዎች በእዉቀትና በጥሩ ስነ ምግባር እንዲታነጹ ለማስቻል ሌሎች መሰል ተቋማትና የተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት በማሳተፍ እየተደረገዉ ያለዉን ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጽህፈት ቤት አማካሪ አቶ የህያ ሱልጣን በበኩላቸዉ የድጋፉ ዋና አላማ ጠያቄ የሌላቸውን የህግ ታራሚዎችን ወገናዊ አለኝታነታችን በማሳየት ታራሚዎች በቆይታቸው እርስ በርስ በመረዳዳትና በመተሳሰብ የበጎነት ባህል እንዲያዳበሩ ለማመላከት ያለመ ነው ብለዋል ።

የህግ ታራሚዎች ነገ ከህብረተሰቡ ጋር ሲቀላቀሉ ከጥላቻ ይልቅ ይቅርባይነትና የመቻቻል እንዲሁም ኢትዮጵያዊነት ባህሎቻችን በተግባር ማስተማር እንዳለባቸውም አሳስበዋል ።

በተቋሙ የተነሱ የግብዓትና የተለያዩ ችግሮችን ለመቅረፍ በቀጣይ ዞኑ በየደረጃው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅቶ ይሰራል ብለዋል።

የወልቂጤ ማረሚያ ተቋም ኃላፊ ተወካይ ምክትል ኮማንደር ጅላሉ በደዊ በርክክቡ ወቅት በሰጡት አስተያየት በጉራጌ ዞን ወጣቶች አስተባባሪነት ጠያቂ ለሌላቸው የህግ ታራሚዎችን እኛ አለንላችሁ በማለት ለተደረገው የቁሳቁስ ደጋፍ ልባዊ ምስጋና መደሰታቸውን ተናግረዋል ።

ድጋፉ ከቁሳቁስነት ባሻገር ታራሚዎች በእዉቀትና በአስተሳሰብ እንዲለወጡና አንባቢ እንዲሆኑ የትምህርት መጽሀፍቶች ድጋፍ ማድረጋቸዉ ለሌሎች ተቀማት አስተማሪ ነው ብለዋል።

በተቋሙ ወስጥ እሰከ 10ኛ ከፍል ቢቻ ትምህርት እየተሰጠ ሲሆን መደበኛ ትምህርት ወደ 12ኛ ክፍል ደረጃ ለማሳደግ አስፈላጊውን መስፈርት ማሟላት እንዲችል በማድረግ ፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር፣ የእርሻ መሬት አቅርቦት
ሌሎች የግብዓት ችግሮች እንዲፈቱላቸው ጠይቀዋል።

አስተያየታቸው ከሰጡን የህግ ታራሚዎች መካከል አቶ ስመኘው አለሙ፣ አቶ አለና ተካ እና ወ/ሮ እለፍነሽ አረብ እንዳሉት በተደረገላቸው የቁሳቁስ ድጋፍና የምክር አገልግሎት ከፍተኛ ደስታ አንደተሰማቸው ተናገረዋል ።

ነገ የተሻለ አምራች ኃይል እንዲሆኑ በማረሚያ ተቋሙ እየተሰጣቸው ያሉ የቀለም፣የሞያና የተለያዩ ትምህርቶች ተጠናክሮ መቀጠል አለባቸው ብለዋል።

ከህብረተሰቡ ጋር ሲቀላቀሉ በተቋሙ የቀሰሟቸውን የወንጀል አስከፊነትና የህግ የበላይነት እንዲሁም የአብሮነትና የመረዳት ባህል የበለጠ እንደሚያጠናክሩ ተናግረዋል ።

በወልቂጤ ማረሚያ ተቋሞ ለሚገኙ ጠያቂ ለሌላቸው የህግ ታራሚዎች ከጉራጌ ዞን አስተዳደር ፣ከገቢዎች ፣ከሠላምና ፀጥታ መምሪያ የተወጣጡ በጎ ፈቃደኞች የተለያዩ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነዉ።

= ኢትዮጵያን እናልማ፣ የፈረሰውን እንገንባ፣ለፈተና እንዘጋጅ!

በመረጃ ምንጭነት ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *