የህግ ታራሚዎች በቆይታቸው በእውቀትና በጥሩ ስነ ምግባር ታንፀው ነገ የተሻለ አምራች ዜጋ እንዲሆኑ የትምህርትና ሌሎች ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ መምሪያ አስታወቀ።

መስከረም 2/2015 ዓ.ም

የህግ ታራሚዎች በቆይታቸው በእውቀትና በጥሩ ስነ ምግባር ታንፀው ነገ የተሻለ አምራች ዜጋ እንዲሆኑ የትምህርትና ሌሎች ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ መምሪያ አስታወቀ።

መምሪያዉ በወልቂጤ ከተማ ማረሚያ ተቋም በተለያዩ ምክንያት በህግ ቁጥጥር ስር ለሚገኙ ታራሚዎች ዜጎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተጀመሩ ማህበረሰቡን የሚጠቅሙ የልማት ስራዎች በአዲሱ ዓመት በተሻለ መልኩ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም ተገለፀ።

የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ መምሪያ ኃላፊ አቶ አብዱ አህመድ በዛሬ እለት በወልቂጤ ከተማ ማረሚያ ተቋም በተለያዩ ምክንያት የህግ ታራሚ ለሆኑ ዜጎች የትምህርት ቁሳቁስ አበርክተዋል።

ታራሚዎች በቆይታቸው በቀለም፣ በሞያና በተለያዩ የሙያ ዘርፎች እውቀቶች አግኝተው እራሳቸውን በማዳበር በጥሩ ስነ ምግባር ታንፀው ነገ የተሻለ አምራች ዜጋ እንዲሆኑ ለማስቻል ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ብለዋል ።

መምሪያው በዞኑ የሚገኙ የግልና የመንግሥት ኮሌጆችን በማስተባበር በችግኝ ተከላ ፣የአቀመ ደካማ ቤት የመገንባትና በሌሎች ዘርፎች ህበሰተሰቡን ተጠቃሚ የሚደርጉ የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት እያከናወኑ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በዛሬው ዕለት 30 ለሚሆኑ በወልቂጤ ማረሚያ ተቋም ለሚገኙ የህግ ተራሚ ተማሪዎች 40 ደርዘን ደብተርና 12 ፖኬት እስክሪብቶ መስጠታቸውን የገለጹት ኃላፊው አቶ አብዱ የዛሬውን ጨምሮ 286ደርዘን ደብተርና 62ፓኬት እሰክርፕት ደጋፍ መደረጉም ጠቁመዋል ።

የወልቂጤ ማረሚያ ተቀም ከመደበኛ ትምሀርት ባሻገር የጀመረው ሙያ ነክ ስልጠናዎች ቀጣይ በተለያዩ በቴክኒክና ሙያ የትምህርት ዘርፎች ከወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመሆን የተጠናክረ ስራ ይሰራል ብለዋል ።

በዞናችን የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች ብቃት ያላቸው ባለሙያዎችን በማፍራት ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት የማይተካ ሚናቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ያጋጠማቸው የሰልጣኞች ቁጥር መቀነስ ችግር ለመቅረፍ የሚመለከታቸው ተቋማት በትኩረት ሊሰሩበት እንደሚገባም ጠቁመዋል።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱ ድንቁ በበኩላቸው በዘንድሮ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በርካታ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ የልማት ስራዎች በአዲሱ ዓመት በተሻለ መልኩ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም ገልጸዋል ።

የህግ ታራሚዎች በእዉቀትና በጥሩ ስነ ምግባር እንዲታነጹ ለማስቻል በቴክኒክና ሙያ መምሪያ የተጀመረው መልካም ተሞክሮ በሌሎች መሰል ተቋማት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

የህግ ታራሚዎች ነገ ከህብረተሰቡ ጋር ሲቀላቀሉ ከጥላቻ ይልቅ የመረዳዳት ይቅር ባይነትና የመቻቻል እንዲሁም ሌሎች ኢትዮጵያዊነት ባህሎቻችን እንዲላበሱ በተግባር ማስተማር ይገባል ብለዋል ።

የወልቂጤ ማረሚያ ተቋም ኅላፊ አቶ ሚስባ ግራኝ ተቋሙ ታራሚዎች በጥሩ ስነ ምግባር ታንፀው የተሻለ ዜጋ ሆኖ እንዲወጡ በቆይታቸው የቀለም ፣የሙያና ተያያዥ ትምህርቶች አየተሠጠ መሆኑን ገልጸዋል ።

በቀጣይ የትምህረት ዘመን ከ1ኛ እስከ10ኛ ከፍል 346 ተማሪ ፣በሞያ 320 ተማሪ በጎለማሳ 51 ተማሪዎችን ለማስተማር መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።

ድጋፍ ከተደረገላቸው ታራሚዎች መካከል አቶ ሙሉጌታ ቸሩና አቶ ታፈሰ ገብረ ማሪያም በማረሚያ ቆይታቸው እየተሰጣቸው ያሉ የተለዬ ትምህርቶች ከሚያገኙት እውነት ባሻገር የባህሪ ለውጥ እንዲያመጡ ድርሻው የላቀነው ብለዋል።

በዕውቀት ዳብረው በቀጣይ ከህበረተሠቡ ሲቀላቀሉ የስራ ዕድል በመፍጠር በተለያዩ መልኩ ወንጀል በመስራት ያስከፋነውን ማህበረሰብ እንድንክስ ይረዳናል ብለዋል።
በተደረገላቸው የትምህርት ቁሳቁስ ከፍተኛ ደስታ አንደተሰማቸው አስተያየት ሰጪ ታራሚዎች ተናግረዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምርያ ነው።

ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *