የህዝብ ሀብትና ንብረት ለታለመለት አላማ እንዳይዉል በመዋቅሮች የሚስተዋለዉን የኦዲት ግኝቶች ወደ መንግስት ተመላሽ እንዲሆኑ ለማድረግ የኦዲት አስመላሽ ግብረ ሃይል ኮሚቴ የተጠናከረ ስራ መስራት እንዳለበትም ተገለጸ።

የካቲ

የጉራጌ ዞን ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ልክነሽ ሰርገማ እንዳሉት የኦዲት ጉድለት አስመላሽ ግብረ ሃይል በዛሬ ዕለት ዉይይት ያደረገ ሲሆን በዚህም ቴክኒክ ኮሚቴዉ ገምግሞ ባመጣው ሪፖርት አብይ ኮሚቴዉ መምከሩንና የውሳኔ ሀሳቦችም እንዳሳለፈ አስረድተዋል።

እንደ ዞናችን መሻገር ያልቻልናቸዉ በርካታ የህዝብ ሀብትና ንብረት ለታለመለት አላማ እንዳይዉል የአሰራር ክፍተት መኖሩም አመላክተዋል።

ኦዲት ተደርገዉ ከታወቁ ጉድለቶች መካከል በአፈር ማዳበሪያ፣ በጥሬ ገንዘብ እንዲሁም የገቢ ጉድለቶች መኖራቸዉም አስረድተዉ እነዚህም ጉድለቶች ለማስመለስ የኦዲት ጉድለት አስመላሽ ግብረሃይ በትኩረት እየሰራ እንደሆነም አብራርተዋል።

ከ2007 ዓ.ም እስከ 2016 ዓ.ም የአንድ ከተማ አስተዳደር ጨምሮ የ11 መዋቅር በመሊየን የሚቆጠር ሀብት የኦዲት ጉድለት ትስተዋልባቸዋል።

የአሰራር ክፍተት አዲት ተደርጎ የታወቀ ሲሆን በጉድለት የተገኘዉ የህዝብ ሀብት ለመንግስት ገቢ መደረግ እንዳለበትም አመላክተዋል።

በጉድለት የተገኘዉ የኦዲት ግኝት ግብረሀይሉ ወደ መንግስት ካዝና እንዲመለስ አጽኖት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነም አስረድተዋል።

የኦዲት ግኝት የተገኘባቸዉ መዋቅሮች በተገቢዉ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸዉም አስረድተዉ ጉድለት አስመላሽ ኮሚቴዉ ከየካቲት 7/2016 አመተ ምህረት ጀምሮ በአካል በመንቀሳቀስ ድጋፍ በማድረግ የጎደሉ ሀብት እንዲመለሱ የማድረግ ስራም እንደሚሰራም አብራርተዋል።

ከኦሞ ባንክ ጋር የሚነሱ ሰፊ ችግሮች መኖራቸዉም አስታዉቀዉ የኦሞ መይክሮ ፋይናንስ ስራ አሰኪያጅ እንደ ግብረሃይሉ ታች ድረስ ወርዶ ለመደገፍና በዘርፉ ያሉ ዉስንነት ለመመልከት መዘጋጀታቸዉም አብራርተዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *