የህብረት ስራ ማህበራት በሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት እድገት ላይ ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ተሳትፏቸውን ለማጠናከር በትኩረት መስራት እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።


የህብረት ስራ ማህበራት በሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት እድገት ላይ ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ተሳትፏቸውን ለማጠናከር በትኩረት መስራት እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።

የአግኖት ኃላፊነቱ የተወሰነ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ዩኒየን ጠቅላላ ጉባኤውን በወልቂጤ ከተማ ተካሄደ።

አግኖት የገንዘብ ብድርና ቁጠባ ህብረት ስራ ዩኒየን በ2005 ዓ.ም. በ2ሺህ 349 የተናጠል አባላት ላይ የተቋቋመ ሲሆን መነሻ ካፒታሉ 120 ሺህ ብር ነበር።

ዩኒየኑ የአባላቱ ቁጥር ከማሳደግ በተጨማሪ የቁጠባ ባህሉ ለማጎልበት እየሰራ ይገኛል።

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ አበበ አመርጋ አግኖት የገንዘብ ብድርና ቁጠባ ህብረት ስራ ዩኒየን የሀብት መጠኑ ወደ 40 ሚሊዮን በማድረስ በዞኑ በ11 ወረዳዎች ለሚገኙ አባላቶቹ የብድር አገልግሎት በመስጠት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን አሳድጎላቸዋ ብለዋል።

ዩኒየኑ በምጣኔ ሀብት እድገት፣ በመልካም አስተዳደር እና በፋይናንስ ላይ ያለው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ የተናገሩት አቶ አበበ ዩኒየኑ የሚሰጠው አገልግሎት ይበልጥ ለማጠናከር የዞኑ አስተዳደር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

የዞኑ ህብረት ስራ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን ነጋሽ በበኩላቸው በዞኑ የሚገኙ ህብረት ስራ ማህበራት ዘመኑን የሚመጥን አገልግሎት ለመስጠት እና ደረጃቸውን ለማሳደግ ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

የዞኑ ህብረተሰብ ያለውን የቁጠባ ባህል ለማሳደግ የቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት ማጠናከር እንደሚገባ አቶ ጌታሁን አሳስበዋል።

የዩኒየኑ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተሾመ ጎሹ ህብረተሰቡ በተለያዩ የስራ ዘርፎች በመሰማራት እኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ የብድር አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ተብለዋል ።

አቶ ግምባሩ ተክሌ የዩኒየኑ ስራ አስኪያጅ ሲሆኑ ዩኒየኑ ዘመናዊ የፋይናንስ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ብለዋል።

የዩኒየኑ የተናጥል አባላት ቁጥር እያደገ መሆኑን የተናገሩት ስራአስኪያጁ የቁጠባ መጠኑ እንዲሻሻል በማድረግ ህብረተሰቡ የብድር ፍላጎቱን ለማሟላት እየተሰራ ነው ብለዋል።

እንደ አቶ ግንባሩ ገለፃ ዩኒየኑ የሴቶች ተሳትፎ ለማጠናከር እየሰራ ሲሆን በተፈጠረላቸው ግንዛቤ ከኢኮኖሚ ጥገኝነት ተላቀው የራሳቸው ሀብት ማፍራት ችለዋል ብለዋል።

አቶ ገብሬ አማኖና ወይዘሮ አለም ወልዴ በሰጡት አስተያየት ሴቶች በቁጠባ ላይ የላቀ ተሳትፎ እንዲኖራቸው በማድረግ ተጠቃሚነታቸው እያሳደገላቸው ይገኛል።

እንደ አባላቱ ገለጻ በብድርና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበር መታቀፋቸው በኑሯቸው ላይ መሰረታዊ ለውጥ አስገኝቶላቸዋል።

በመሆኑም ዩኒየኑ የማበደር አቅሙ ለማሳደግ እና ወደ ባንክ ደረጃ ለማሸጋገር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

በመጨረሻም በበጀት አመቱ የተሻለ ተሳትፎና እንቅስቃሴ የነበራቸው ህብረት ስራ ማህበራት፣የመንግስት ተቋማት እና ዩኒየኖች እውቅና ተሰጥቷቸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው ።

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *