የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚሊሻ አባላት ማጠናከር እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ሚሊሻ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ታህሳስ 09/2015 ዓ.ም

የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚሊሻ አባላት ማጠናከር እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ሚሊሻ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የጉራጌ ዞን ሚሊሻ ጽህፈት ቤት የ2015 አመተ ምህረት የግማሽ አመት እቅድ አፈጻጸም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ ገምግሟል።

የሚሊሻ አባላት በማጠናከር በየአካባቢዉ ሰላም በማስከበር እንዲሁም በዘርፉ የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት ጠንካራ ተቋም መገንባት ይገባል።

የጉራጌ ዞን ሚሊሻ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብድልሀፊዝ ሁሴን እንዳሉት የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅዶችን ለማሳካት የሚሊሻ አካላት ማጠናከርና በዘርፉ የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት ጠንካራ ተቋም መገንባት ይገባል።

የአከባቢያችን ሰላምና ጸጥታ በማስከበር የህብረተሰቡን እርካታ ማሳደግ እንደሚገባ ጠቁመው ለዚህም ከባለድርሻ አካላት ጋር የተጠናከረ ስራ መስራት ይኖርብናል ብለዋል።

አሁን ላይ ያለው የሚሊሻ ሀይል ከተቀመጠው መስፈርት አንጻር ውስንነት መኖሩን የገለጹት ኃላፊው በማህበረሰቡ ተሳትፎ አዳዲስ የሚሊሻ አካላትን በመልመል የአገልግሎት ተደራሽነት ለማሳደግ መሰራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

እንደ ኃላፊው ገለጻ ለአዳዲስና ለነባር ሚሊሻዎች በየጊዜው እቅማቸውን መገንባት እንዳለበት ጠቁመው በተግባራቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ህብረተሰቡና መንግስት በማስተባበር አስፈላጊውን ግብአት ማሟላት ያስፈልጋል ብለዋል።

መረጃን በተገቢውና በወቅቱ ተንትኖና አደራጅቶ ለሚመለከተው አካል ተደራሽ ከማድረግ አንጻር ውስንነት መኖሩን አመላክተው በቀጣይ እነዚህና መሰል ችግሮችን ለመቅረፍ መስራት ይኖርብናል ብለዋል።

ከሰው ሀይል ጋር ተያይዞ ያለውን ውስንነት ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚሰራም አቶ አብድልሀፊዝ ጠቁመዋል።

በአከባቢ ሰላምና ጸጥታ ጥበቃ ዙሪያ ለህብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ የመፍጠር ስራ መሰራቱን ተጠቁሞ በዚህም ማህበረሰቡ ከሚሊሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ሲከሰት ለጸጥታ አካላት ጥቆማ መስጠት፣ ለሚሊሻ አካላት የደንብ ልብስ መግዣ ገንዘብ መስጠትና ወንጀለኛን አሳልፎ በመስጠት አጋዥ ህብረተሰብ መፍጠር መቻሉን በሪፖርቱ ተጠቅሷል።

በህብረተሰብ ተሳትፎ አዳዲስ ሚሊሻዎች የመመልመልና ለነዚህም የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና መሰጠቱንም ተመላክቷል።

ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ለ1ሺህ 847 የዘማች ቤተሰቦች የተለያዩ የገንዘብና የአይነት ድጋፍ መደረጉን ጠቁመው ይህም በብር ሲተመን 5 ሚሊዮን 796 ሺህ 885 ብር መሆኑን ተገልጿል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በተግባር አፈጻጸም ወቅት ያሉ ውስንነቶችን ለመቅረፍ በቀጣይ እንደሚሰሩም ተናግረዋል።
አስተያየት ሰጪዎቹ አክለውም የሰው ሀይል ከማሟላትና ከማብቃት ጋር ተያይዞ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

በአከባቢ ጸጥታ ዙሪያ ለህብረተሰቡን ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እንደሚሰሩ ገልጸው አዳዲስ የቀበሌ የሚሊሻ ሀይል ለመልመልና ለማጠናከር እንደሚሰሩም ጠቁመዋል።

የአከባቢያቸውን ሰላምና ጸጥታ ለማረጋገጥ ህብረተሰቡን በማሳተፍና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰሩ እንደሆነም አመላክተዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *